ኢዜማ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮች ጥቆማ መቀበያ ቀነ ገደብ እንዲራዘም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጻፈው ደብዳቤ መጠየቁን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባሰራጨው መግለጫ ጠይቋል።
ፓርቲው ጊዜው እንዲራዘም የጠየቀው፣ ሕዝቡ በተለያዩ አጀንዳዎች ተጠምዶ በመክረሙ ስለኮሚሽኑ እና አገራዊ ምክክሩ በቂ ግንዛቤ አለመያዙን፣ መገናኛ ብዙኀን በአገራዊ ምክክሩ ዙሪያ ሕዝቡን ለማንቃት ቁልፍ ሚና አለመጫወታቸውን እና በጥቆማ አሰጣጡ ውስብስብነት ሳቢያ ሕዝቡ፣ ፖለቲካ ፓርቲዎች እና ሲቪክ ማኅበራት በቂ ጊዜ አለማግኘታቸውን በመጥቀስ ነው።
የዕጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማ መቀበያ ጊዜ በመጭው ዓርብ እንደሚጠናቀቅ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀደም ሲል ማስታወቁ ይታወሳል።