ኢትዮጵያውያን በአዲስ አበባ አሜሪካ ኤምባሲ ደጃፍ የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰሙ ።

አሜሪካ ኢትዮጵያ ሉአላዊትና የራሷን እድል በሪሷ የምትወስን ሀገር መሆኗን በመዘንጋት እያደረገች ያለው እጅ ጥምዘዛ በመላው ኢትዮጵያውያን ዘንድ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን በመገንዘብ እጇን ልትሰበስብ ይገባል ሲሉ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዝዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ አሳስበዋል፡፡ የኢትዮጵያ ማደግ አሳስቧት ተገዳዳሪ ኃይልን በማጀገን ኢትዮጵያን የማፍረስ እኩይ ሴራ እየሰሩ ያሉ አንዳንድ ምእራባውያን ሀገራትን መስማት እንደማይገባም ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም ኢትዮጵያ ለአሜሪካ ጣልቃ ገብነት በጅ የማትልና ለዘመናዊ ቅኝ ግዛት የማትንበረከክ ሀገር መሆኗን ለማስረገጥ በአሜሪካ እንዲሁም እንግሊዝ ኤምባሲ መፈክሮችን ያነገቡ ኢትዮጵያውያን በመጓዝ ላይ ይገኛሉ:: የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጥምረት ለኢትዮጵያ ህዝብ ያዘጋጀው “ከኢትዮጵያ ላይ እጃችሁን አንሱ!! ፤ የውጭ ጣልቃ ገብነትን አንቀበልም!!” የሚል ሰላማዊ ሰልፍ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
May be an image of 5 people, people standing and road
May be an image of 1 person, standing and outdoors