ሩስያ ኢትዮጵያ የሚኖሩ ዜጎቿን የማስወጣት ዕቅድ እንደሌላት አስታወቀች።

ሩስያ ኢትዮጵያ የሚኖሩ ዜጎቿን የማስወጣት ዕቅድ እንደሌላት አስታወቀች። በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ ባወጣው መግለጫ አዲስ አበባ እንደሁል ግዜው ሰላም ናት ብሏል።“በአዲስ አበባ ያለው ሁኔታ የተረጋጋ ነው። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁ በዋና ከተማይቱ የዕለት ተዕለት የኑሮ ዘይቤ ላይ ምንም አይነት ለውጥ አላመጣም። ኤምባሲው እንደተለመደው መስራቱን ቀጥሏል። ቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት እንደተለመደው እየሰራ ነው።“ ሲል ገልጿል።የአሜሪካ አየር ተቆጣጣሪ ተቋም በቅርቡ የኢትዮጵያ አየር ክልል አደጋ ተደቅኖበታል በማለት ካሰራጨው መረጃ በተቃራኒው የኢትዮጵያ አየር ክልል ፍጹም ሠላማዊ መሆኑን በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ በመግለጫው ገልጿል።