በደብረ ብርሃን ከተማ ከነገ ጀምሮ የከተማው መታወቂያ ካላቸው ግለሰቦች ውጪ በቀን እንቅስቃሴ ማድረግ ተከለከለ

በደብረ ብርሃን ከተማ ከነገ ህዳር 16 ቀን 2014 ጀምሮ የደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪዎችና የደብረ ብርሃን ከተማ መታወቂያ ካላቸው ግለሰቦች ውጪ በከተማው ውስጥ በቀን እንቅስቃሴ ማድረግ እንደማይቻል የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ፡፡

ውሳኔው የከተማው በተለያዩ አካባቢዎች ሰርጎ ገቦች ገብተው አካባቢን የማጥናትና መረጃ የመስጠት ሥራ እየሰሩ እንደሆነ ስለተደረሰበት ሰርጎ ገቦችን መለየትና አካባቢውን ከሰርጎ ገቦች ነጻ ለማድረግ የተወሰነ መሆኑ ተገልጿል።

ስለሆነም ለከተማውና ለነዋሪዎች ደህንነት ሲባል በከተማው በየትኛውም አካባቢ የደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪና መታወቂያ ካላቸው ሰዎች ውጪ በቀን እንቅስቃሴ ማድረግ የማይቻል መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በደብረ ብርሃን ከተማ የተጠለሉ ወገኖችም በተዘጋጀላቸው መጠለያ እንዲገቡ ከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡