12 የሕወሓት ከፍተኛ የጦር መሪዎች ተደመሰሱ

  • የኢትዮጵያ መንግሥት ጦሩን ከዛሬ ጀምሮ ወደ ከፍተኛ የማጥቃት እርምጃ ውስጥ አስገባ፡፡
  • በባቲ ግንባር 6 የሽብር ቡድኑ የአርሚና ኮር አመራሮች ተደመስሰዋል፡፡
  • የተደመሰሱት መሪዎች በሕግ ሲፈለጉ የነበሩ ናቸው፡፡
  • በከሚሴ ግንባርም በተመሳሳይ የጠላትን ጦር ሲመሩ የነበሩ 6 አመራሮች ተደምስሰዋል፡፡
  • ይህን ያሳወቁት የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) አሁን በሰጡት መግለጫ ነው፡፡

“ባለፉት 2 ቀናት በባቲ ግንባር በተደረገ ልዩ ኦፕሬሽን 6 የአርሚና እና የኮር ከፍተኛ አመራሮቹ ተደምስሰዋል። እነዚህ አመራሮች በፌዴራል መንግስት በሀገር ክህደት ወንጀል ሲፈጉ የነበሩ ከሃዲ ጄነራሎች እና ኮሎኔሎች ናቸው።” ብሏል የመንግስት ኮሚኒኬሽን ዛሬ ምሽት በሰጠው መግለጫ፣ በመግለጫው ላይ ተደመሱ የተባሉት ጄነራሎችና ኮሎኔሎች ስም አልተገለፀም።

በተጨማሪ በከሚሴ ግንባር በተለያዩ ቦታዎች በተደረጉ ልዩ ኦፕሬሽኖች የጠላትም ግንባር ጦር ሲመሩ የነበሩ 6 ከሃዲ ከፍተኛ የጦር አመራሮች ከነጠባቂዎቻቸው ተደምስሰዋል።

በዛሬው ዕለት በባቲ ግንባር በተደረገው ከፍተኛ የማጥቃት እርምጃ ቀደም ሲል ከነበሩት ጥቃቶች ተርፎ ለዳግም ማጥቃት ተዘጋጅቶ የነበረው የጠላት ኃይል የተደመሰሰ ሲሆን እግሬ አውጪኝ ብሎ ወደ ኃላ እየፈረጠጠ ያለውን ጠላት እግር በእግር የወገን ኃይል እየተከተለ እያፀዳው ይገኛል።

በሌሎች ግንባሮችም የወገን ጦር በሰነዘረው ከፍተኛ ማጥቃት ጠላት በከፍተኛ ደረጃ እየተመታ ይገኛል። በዚሁ አጋጣሚ የወገንን ክንድ መቋቋም አቅቶት በተናጠል እና በቡድን እየሸሸ የሚገኘውን የጠላት ኃይል ዘረፋ እንዳይፈፅም እና ንብረት እንዳያወድም ህብረተሰቡ ተደራጅቶ አካባቢውን እንዲጠብቅ መንግስት ጥብቅ ጥሪ ያቀርባል። እንዳሁም እየሸሸ ያለው ጠላት እጁን እንዲሠጥ የማይሰጥ ከሆነ ህብረተሰቡ ተደራጅቶ አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስድ መንግስት ያስገነዝባል”