ወራሪው የህዋሃት ቡድን በ360 ዲግሪ ቀለበት ውስጥ ተከቧል!

ወራሪው የህዋሃት ቡድን በ360 ዲግሪ ቀለበት ውስጥ ተከቧል!

አሸባሪውና  የህዋሃት ቡድን በጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ፣ በአማራ ልዩ ኃይል ፣ በፋኖ እና በሚሊሻው በ360 ዲግሪ ቀለበት ውስጥ መከበቡን በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ገብረ ጻድቅ ገልጸዋል።

እኔ ያልመራኋት ሀገር ትፍረስ በሚል እኩይ ሴራ አሸባሪው በድን በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች የመንግሥት ተቋማትንና የግለሰቦችን ሀብትና ንብረት በመዝረፍ ወደር የለሺ ጥፋት እየፈጸመ የሚገኝ ቢሆንም የዘረፈውን ሀብት ይዞ መውጣት እንደማይችል ተናግረዋል።

አካባቢያቸውን ባለማስደፈረስ ህዋሃትን እስከ መጨረሻው በመፋለም ጀብዱ እየፈጸሙ ለሚገኙ ለራሳ አርሶ አደሮች ፣ ለሸዋ ሮቢት ፋኖዎች በተለያዩ ግንባሮች እየተፋለሙ ለሚገኙ አካላት እውቅና ሰጥተዋል።

ወደ ሸዋ ምድር መግባት ይቻላል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው እዚሁ ሸዋ ምድር ላይ ግብአተ መሬቱ ይፈጸማል ፣ በ360 ዲግሪ ቀለበትም ውስጥ ገብቶ የሚገኝ በመሆኑ ኅብረተሰቡ ከስጋት ነጻ ሆኖ አካባቢውን በንቃት እንድጠብቅና ድጋፉን አጠናክሮ እንድቀጥል አሳስበዋል።

አሸባሪ ቡድን በአማራን ሕዝብ ላይ ዘር የማጥፋት ፣ አካላዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ስነ-ልቡናዊ ጥቃት እንደፈጸመ የተናገሩት አቶ ታደሰ ነጻነት ያለመስዋዕትነት ስለማይገኝ አቅም ያለው ሁሉ እንድዘምትና ሌላው የስንቅና ሌሎች ድጋፍ ማድረግ አለበትም ብለዋል።

አርሶ አደሩን ሹመኞችን ብቻ ነው የምንፈልገው በማለት እያታለሉ እንደሚገኙ የጠቆሙት አስተዳዳሪው ገዳዩ አሸባሪ ቡድኑ ግን ማንንም የማይመርጥና ለማንም ወደ ኋላ የማይመለስ መሆኑን አመላክተዋል።

በዘመቻው ላይ የመንግሥት ከፍተኛ ባለ ሥልጣናት ፣ታዋቂ ግለሰቦች ፣ የሃይማኖት አባቶችና አርቲስቶች እየተሳተፉ ሲሆን በአጭር ቀናትም ጁንታውን ወደ መቃብር በመክተት ድል እንቀዳጃለን ብለዋል።