የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች 11ኛ ክልል ሆኖ በይፋ ተመስርቷል።

May be an image of one or more people and people standing11ኛው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ ክልል ህገ መንግስትም በምክር ቤቱ አባላት በሙሉ ድምፅ ፀድቋል።

የምክር ቤቱ አባላትም ቃለ መሀላ ፈፅመዋል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የስራ ቋንቋ አማርኛ እንዲሆን በሙሉ ድምጽ ፀድቋል።

የዞን መዋቅሮች ደግሞ የራሳቸውን ቋንቋ እንደሚገለገሉ ተገልጿል።

የስልጣን እርከን ፍትሃዊነትን በተመለከተ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ፣ አፈጉባኤየክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚዳትና የብሄረሰብ ምክር ቤት አፈጉባኤ በአንድ ጊዜ ከተመሳሳይ ብሄር እንዳይሆኑ ተቀምጧል።

የስልጣን ገደብም የተቀመጠ ሲሆን÷ በተለያየ ምክነያት ከጊዜያቸው ቀድሞ ሊለቁ መቻላቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ረጅም ጊዜ ቢቆዩ ከ10 ዓመት እንዳይበልጥ ተመላክቷል።

May be an image of 2 people, people standing and indoorየብዝሓ ማዕከል ወይንም ዋና ከተማ እንዲኖርም ተደንግጓል፣ የትኞቹ ከተሞች እንደሚሆኑ በዝርዝር ህግ በም/ ቤት እንዲወሰንም በህገ መንግስቱ መጠቀሱን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋገሾ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ ክልል ም/ርዕስ መስተዳደር ሆነው ተሾሙ።

ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋገሾ በክልልና በሀገር ደረጃ በተለያዩ የሀላፊነት ቦታዎች የሰሩ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት የውሃና መስኖ ሚንስቴር ዴኤታ ሆነው በማገልገል ላይ ነበሩ።

ም/ርዕስ መስተዳደሩ በጉባኤው አባላት ፊት ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።

May be an image of 1 person and indoor