የኢትዮጵያ ሀይሎች የማጥቃት እርምጃ በሁሉም ግንባሮች ጀመሩ

በጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ አብይ አህመድ ቀጥተኛ ትዕዛዝ የሚመራው የኢትዮጵያ ህዝባዊ ሰራዊት በሁሉም ግንባሮች ስራውን ጀምሯል! ዛሬ ሌሊት በተደረገው የአየር ድብደባ 9 መኪና ሙሉ የህወሓት ወራሪ ኃይል በቀወት ወረዳ በቀወት ቀበሌ በዶራሠሜት አድርጎ ወደ ሌባ መሥቀያ ሲጏጏዝ የነበረው የህወሓት ወራሪ ኃይል በሰማይ ላይ ንስሮች ንፍሮ ሆኗል!

ሞላሌ ላይ በተወሰደ የአየር ድብደባ 3 መኪና ሙሉ የጠላት ጦር ጭቃ ሆኗል! በምስራቅ ዕዝ ንስሮችና የበረሃ አናብስቱ የአፋር ህዝባዊ ሰራዊት ጥምር ጦር ከባቲ ወደ ኮምቦልቻ አቅጣጫ የትግሬ ወራሪን እንደ ቅጠል እያረገፈው ግስጋሴውን ቀጥሏል! የባቲ ከተማ ምናልባትም ዛሬ ወይም ነገ በወገን ጦር ስር እንደምትወድቅ ወታደራዊ መረጃዎች ይጠቁማሉ!

ከትናንት ከሰዓት ጀምሮ ሁሉም የኢትዮጵያ ሀይሎች የማጥቃት እርምጃ በሁሉም ግንባሮች እንደጀመሩና የሚገኙ ድሎችን ግንባር ካሉ መረጃ ምንጮቻችን ቶሎ ቶሎ እናቀብላችኀለን፤ ለዚህ ዘመቻ ስኬታማነት ሁላችንም የበኩላችንን እንወጣ ስንቅ እናቀብል መረጃ ለወገን ጦር እናድርስ የወገንን እንቅስቃሴ ለሚዲያ አናውለው ምክንያቱም ጠላትን ይጠቅማልና ጠላት የወጣ የወረደበትን ሁሉ የሰው ሀይሉንና ትጥቁን አይነትና ብዛት ማዲያ ላይ እናስጣበት ሁሌም ከወገን ጦር ስኬት አንፃር እንስራ።