በወለጋ በጅምላ ከተጨፈጨፉት ሰዎች በተጨማሪ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የአማራ ተወላጆች ህይወታቸው ለአደጋ ተጋልጧል !

ሰሞኑን በወለጋ የተካሄደውን ማንነት ላይ ያተኮረ ጭፍጨፋና ማፈናቀል ተከትሎ በማሕበራዊ ሚዲያ የተለያዩ አስተያየቶች የተሰጡ ሲሆን መንግስት በወለጋ የሚፈጸሙ ጭፍጨፋዎችን ለምን ማስቆም ተሳነው? የሚል ጥያቄ የቀረበ ሲሆን በወለጋ ለሚጨፈጨፉት የአማራ ብሔር ተወላጆች ተጠያቂውስ ማነው? ሕዝብ ከቀናት፣ ከሳምንታት በፊት ጀምሮ ያለውን አደጋ ይናገራል። “ድረሱልኝ” ይላል! የሚደርስ የመንግስት አካል የለም! ተብሏል።

ከማሕበራዊ ሚዲያ ያነበብናቸውን የተለያዩ ድምጾችን እንደሚከተለው አቅርበናል።

May be an image of 2 people, sunglasses and indoorየሰብዐዊ መብት ተሟጋቹ አቶ ያሬድ ሃይለማርያም በፌስቡክ ገጻቸው እንደከተቡት ” መንግስት በወለጋ የሚፈጸሙ ጭፍጨፋዎችን ለምን ማስቆም ተሳነው? እሺ መንግስት በሰሜኑ ጦርነት ተወጥሮ ነው ቢባል እንኳ የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናትስ በተደጋጋሚ ኦነግ-ሽኔን በአጭር ጊዜ ማጥፋት እንችላለን ሲሉ እየተደመጠ ታዲያ ምን ያዛቸው? በክልሉ ውስጥ ስልጠና የተሰጠው በአሥር ሺዎች የሚቆጠር ልዩ ሃይል የዜጎችን ደህንነት መጠበቅ ካልቻለ ሥራው ምንድን ነው? በወለጋ ለሚጨፈጨፉት የአማራ ብሔር ተወላጆች ተጠያቂውስ ማነው? ሰሞኑን በጅምላ ከተጨፈጨፉት ሰዎች በተጨማሪ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የአማራ ተወላጆች በዚሁ አካባቢ ህይወታቸው ለአደጋ መጋለጡን ከአካባቢው የወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ማነው የሚታደጋቸው? የፌደራል መንግስት እና የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት ዜጎችን ከጥቃት የመታደግ ሃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል። ” ብለዋል አቶ ያሬድ ሃይለማርያም

No photo description available.የኢትዮጵያ ሰብዐዊ መብቶች ኮሚሽን በበኩሉ ኦሮሚያ ክልል: ግድያ እና መፈናቀል በምስራቅ ወለጋ” በድረ ገፁና በማHበራዊ ሚዲያ በለቀቀው መግለጫ ላይ ኢሰመኮ የፌዴራልና የክልሉ መንግስት የፀጥታ ኃይሎች በኪራሙ ወረዳ ላለው የፀጥታ ስጋት ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት እና በነዋሪዎች ላይ በተደጋጋሚ ጥቃት የሚያደርሱ ኃይሎችን ከሕግ ፊት ለማቅረብ ተጨባጭ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ሲል አሳስቧል ። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በምስራቅ ወለጋ ዞን፣ ኪራሙ ወረዳ የሚገኙ ሲቪል ሰዎች ለደኅንነታቸው አስጊ ሁኔታ ላይ የሚገኙ መሆናቸው የሚያሳስብ መሆኑን ገለጸ። በዚሁ ወረዳ፣ ቦቃ ቀበሌ መስከረም 7 እና 8 ቀን 2014 ዓ.ም. በደረሱ ሦስት ተያያዥ ጥቃቶች በአጠቃላይ 18 ሲቪል ሰዎች መገደላቸውን፤ እንዲሁም መስከረም 8 ቀን 2014 ዓ.ም. በውልማይ ቀበሌ በተፈጸመ ሌላ ጥቃት 11 ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ለኮሚሽኑ አሳውቀዋል።  በኪራሙ ወረዳ ባለው አሳሳቢ የፀጥታ ሁኔታ ምክንያት ከተለያዩ የወረዳው አካባቢዎች ተፈናቅለው በኖሌ ቀበሌ፣በሀሮ እና ኪራሙ ከተሞች ተጠልለው የሚገኙ ከ40 ሺህ በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎች ለወራት አስቸኳይ ሰብአዊ እርዳታና ሌሎች ድጋፎችን ባለማግኘታቸው አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ነዋሪዎች አክለው ይናገራሉ። በአሁኑ ወቅት ኪራሙ ወረዳን ከቡሬና ነቀምቴ ከተሞች ጋር የሚያገናኙ ዋና ዋና መንገዶች ለተሸከርካሪ እንቅስቃሴ ተዘግተው እንደሚገኙ ኮሚሽኑ አረጋግጧል። ሲል ገልጿል በመግለጫው !

አማራ በወለጋ ምድር መጨፍጨፍ ከጀመረ ከሶስት አመት በላይ ሆኖታል።እስካሁን አድበስብሶ ከማለፍ ውጭ በወለጋ ምድር የሚካሄደውን የዘር ጭፍጨፋ ያወገዘ የመንግስት አካል፤አባገዳ ወይም የሀይማኖት መሪ የለም። ብለዋል አቶ ሙሳ የተባሉ የፌስቡክ ተጠቃሚ። ሌላው አቶ ታርቆ ፈንታው ወለጋ ላይ የሚፈጸመውን እልቂት ማስቆም አቅቷቸው አይደለም። ፍላጎቱ ቢኖርና ዐቅም ቢያጥር እንኳ እራሳቸውን እንዲከላከሉ ማድረግ ይችሉ ነበር ብለዋል።

መንግስቱ ሙሴ የተባሉ ጸሃፊ የሚከተለውን ጽሁፍ በፌስቡክ ገጻቸው አስፍረዋል።

ወለጋ እና መተከል
==========
May be an image of textየኦሮሚያ ክልል አስተዳደር እና ቤሻንጉል ተብሎ በህወሓት የተሰራው ክልል በአማሮች ላይ የሚካሄደውን ፍጅት ለማስቆም ተሳናቸው ብለን ብንጠይቅ መልስ የሚኖር አይመስለኝም። መጀመሪያ በቀሪ የኦሮሚያ ዞኖች እና ቀበሌወች ቦግ እልም ከሚለው ዘር ላይ ያነጣጠረ ግድያ እና ማፈናቀል ጋብ ብሎ በወለጋ ብሎም በሆሮ ጉድሩ አውራጃ ከዚያም ጠበብ ብሎ በአሙሩ ኪረሙ ወረዳ የዘር ጭፍጨፋው ቀጥሏል።
በዚሁ ክፍለሀገር ለትምህርት የሄዱ ወጣት ልጆች መዳረሻቸው ጠፍቶ እንደቀረም የምናውቀው ነው እናም ለምን እና እንዴት የክልሉ አስተዳደር ቀጣይ የዘር ፍጅቱን ለማቆም ተሳነው? ገምቶ ለመናገር ይከብዳል ግን አንድ ነገር ግልጽ እየሆነ የመጣ ጉዳይ የክልሉ የጸጥታ ኃይል ይህን ቀርቶ ሌላ ኃይልን ማቆም እንደሚችል ለመረዳት በየግዜው ሰልጥነው የተመረቁ የልዩ ኃይል አባላቱን እና በክልሉ ያለውን የጦር ብቃት አንድ ሁለት ተብሎ የሚቆጠር በመሆኑ ወንጀሉ የጋራ ጥቅም አለው ቢባል ተገቢም ተጨባጭ ተያያዥ ማስረጃወች ማቅረብ ይቻላል። ሕዝብ እና ነዋሪው እንግዲህ ይህን የክልሉ አስተዳደርን ቀጣይ ወንጀል ተረድቶ እና አውቆ ለቀጠለው የዘር ፍጅት መፍትሄው እራስን መከላከል መሆኑን በክልሉ የሚኖሩ የተማሩ ወጣቶች እና የዚህ የዘር ፍጅት ሰለባ የሆነው አባላት ለወገኖቻቸው ሊያስረዱ ይገባል። እራስን መከላከል ፍትሀዊም የግል ግዴታም መሆኑን አውቆ በዝምታ ከመታረድ የተሻለ አማራጭ እና ዋነኛም መፍትሄ መሆኑን ጥቃቱ ለተነጣጠረበት ህዝብ ማሳየት ያስፈልጋል።
ሌላው የኢትዮጵያ ሰበአዊ መብጥ ጠባቂ ማሕበር አለማቀፍ ትኩረት እንዲሰጠው ተግቶ ሊሰራ እና የራሱን ኃላፊነት በአግባቡ ሊወጣ ይገባል። አማራውን እንወክላለን ብለው የተደራጁ ድርጅቶች ስራ እና ተግባር ምን ሊሆን ይችላል። የሚያሳዝነው በሕዝብ ስም መደራጀት እና ሕዝብን እስከ መሰዋ’እትነት ማገልገል በሀገራችን የዚህ ዘመን ፈሊጥ እና የእንጀራ ማግኛ የኑሮ ማደላደያ ሆኖ መገኘቱ ነው። ሕዝብ እየረገፈ በስሙ ተደራጀን የሚሉት የመፍትሄ ሀሳብ ማቅረብ። በቦታው ተገኝተው ሕዝብን ማተባበር እና ከወንጀል እራሱን እንዲከላከል መምከር እንኳን የማይችሉ ሆነው ሲገኙ ካማሳዘን ባለፈ አሳፋሪ እና የታሪክ ምፀት ነው።
መፍትሄው እንደምናየው ከክልሉም ሆነ ከፌደራሉ መፍትሔ የለውም። አሁን የሰበአዊ መብት ተሟጋቾች እና ሕዝብ እራሱን እንዲከላከል መምከር አማራጭ የለሽ ብቸኛ መፍትሄ ስለሆነ እባካችሁ ዝምብሎ መታረድ ይቁም እራስህን ተከላከል መክት! ይህ በሰሜን ወሎ ላለውም ተጨማሪ አማራጭ መሆኑ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። ፊጣሪ ከተበደሉት እና ለጥቃት ከተጋለጡት ጎን ይቁም ሲሉ መንግስቱ ሙሴ ወደ ፈጣሪ ተማጽነዋል።
በርካቶች በወለጋ እየተጨፈጨፉ ስላሉት የአማራ ተወላጆች መንግስት አፋጣኝ መፍትሔ እንዲፈልኛ እርምጃ ወስዶ ጥቃቱን እንዲያቆም የጠየቁ ሲሆን የአማራ አክትቪስቶች የትዊተር ዘመቻ ጠርተዋል። በትዊተር ዘመቻው በወለጋ ያሉ ወገኖች ድምጻችን ያስፈልጋቸዋል። በማለት ዛሬ ምሽት ከ2:00 ጀምሮ የትዊተር #StopAmharaGenocide መርሃግብር እንዳላቸው ይፋ አድርገዋል።
No photo description available.ኢዜማ ባወጣው መግለጫ በምስራቅ ወለጋ እና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖች በንፁሃን ዜጎች ላይ የሚፈፀመውን ጥቃት በአስቸኳይ ማስቆም እንደሚገባ ጠይቋል ። ፓርቲው በይፋዊ የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ትስስር ገጹ ባወጣው መግለጫ በምስራቅ ወለጋ ዞን እና አካባቢው ማንነትን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች የንጹሃንን ህይወት እየቀጠፉ ነው። በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪራሙ ወረዳ ሀሮ ቀበሌ እንዲሁም በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አቤ ደንጎሮ እና ሆሮ ወረዳዎች በሚገኙ ቀበሌዎች ጥቃቶች እየተፈጸሙ መሆኑን ገልጿል።

በዚህም «በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ሎሚጫ፣ ቱሉሞቲ፣ ቦቶሮ፣ ቦራ፣ ወለጌ፣ ትጌ፣ ኮትቻ፣ ጋሬሮ፣ ጎርቴ፣ አርቡ ሲንታ፣ አርቡ ሶቴ፣ ገበርጉን 2ኛ፣ ኢዶ ቦቲ እና ሌሎች አከባቢዎች በሚኖሩ ንፁሃን ዜጎች ላይ ማንነታቸውን መሰረት አድርጎ» « እየተፈፀመ የሚገኘው አሰቃቂ ጥቃት ጊዜ እየጠበቀ እያገረሸ አሁንም የወገኖቻችንን ውድ ሕይወት እየቀጠፈ ይገኛል።» ብሏል።ከዚህ ቀደም በአካባቢዎቹ የሚኖሩ ዜጎች በማንነታቸው ምክንያት ብቻ የጥቃት ስጋት እንደበረባቸው ለየአካባቢው መስተዳድር ቢያመለክቱም ባለስልጣናቱ «በቁጥጥራችን ስር ነው ወይም የሚያሰጋ ነገር የለም» «እያሉ ብዙ ወገኖችን አጥተናል። » ብሏል።

መንግሥት በአካባቢው ያለውን የአስተዳደር መዋቅር እንዲፈትሽ በተደጋጋሚ ቢያሳስብም ይህ ነው የተባለ የማስተካከያ እርምጃ አለመወሰዱን እና ጥቃቶችም ተጠናክረው መቀጠላቸውን ፓርቲው በመግለጫው አመልክቷል። በአካባቢው የሚገኙ የጸጥታ ኃይሎች ሕዝቡን መከላከል ቀርቶ ራሳቸውም የጥቃቱ ሰለባዎች መሆናቸውን በስፍራው ተገንቶ መመልከቱን ኢዜማ ገልጿል። በአካባቢው የመጓጓዣ አገልግሎቶች በመቋረጣቸው የሕክምና አገልግሎትን ጨምሮ ሌሎች ማሕበራዊ አገልግሎቶች መስተጓጎላቸውን ፓርቲው ጠቅሷል። ሁኔታው የነዋሪዎችን ሕይወት እንዳከበደባቸው የገለጸው ፓርቲው የክልል እና የፌዴራል የጸጥታ ኃይሎች ችግሩን በቁጥጥር ስር ማዋል ያልቻሉበትን ሁኔታ እንዲያስረዱ ጠይቋል። ነዋሪዎች ከደህንነት ስጋት ተላቀው መደበኛ ሕይወታቸውን መግፋት እንዲችሉ መንግስት ዘላቂ መፍትሔ እንዲሰጥበትም ፓርቲው በመግለጫው ጠይቋል።
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ባወጣው መግለጫ በበኩሉ የዜጎችን ሰላምና ደኅንነት ከማስጠበቅ የሚቀድም አንዳችም መንግሥታዊ ተግባር ሊኖር አይገባም ብሏል፡፡ በዞኑ ዘር ተኮር የሆነ ጭፍጨፋ ሲፈፀም መቆየቱን የገለፀው አብን ‹‹በምስራቅ ወለጋ ያለው ሁኔታ መቋጫ አልባ ሆኖ ከጊዜ ወደጊዜ የሚፈፀመው እልቂትና ማፈናቀል ተጠናክሮ ቀጥሏል›› ሲል ነው የመንግሥትን አስቸኳይ ትኩረት የጠየቀው፡፡ መንግሥት በድርጊቱ ፈፃሚዎች ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንዲወስድ፣ ለተጎጂዎችና የተጎጂ ቤተሰቦች ተገቢው ድጋፍ እንዲደረግና በአስቸኳይ ፍትሕ እንዲሰፍን ሲልም ጠይቋል፡፡
ኢሰመኮ የፌዴራልና የክልሉ መንግስት የፀጥታ ኃይሎች በኪራሙ ወረዳ ላለው የፀጥታ ስጋት ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት እና በነዋሪዎች ላይ በተደጋጋሚ ጥቃት የሚያደርሱ ኃይሎችን ከሕግ ፊት ለማቅረብ ተጨባጭ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ያሳስባል። በተጨማሪም በግጭቱ ምክንያት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ሰዎችን ወደ ቀያቸው መመለሱ እንደተጠበቀ ሆኖ ተፈናቃዮቹ ለከፋ የሰብአዊ ቀውስ ከመጋለጣቸው በፊት በአፋጣኝ ወረዳውን ከሌሎች አከባቢዎች የሚያገናኙ መንገዶች እንዲከፈቱና አስፈላጊው ሰብአዊ እርዳታ መድረሱን እንዲያረጋግጡ ኢሰመኮ በጥብቅ ያሳስባል።
ወለጋ!
ሕዝብ ከቀናት፣ ከሳምንታት በፊት ጀምሮ ያለውን አደጋ ይናገራል። “ድረሱልኝ” ይላል!
የሚደርስ የመንግስት አካል የለም!
በተፃፈም ባልተፃፈም ሕገ መንግስት፣ የዜጎችን በሕይወት የመኖር፣ የአካል ደሕንነት ማስጠበቅ ግዴታ ነው። አንድ አገር የሚፅፈው፣ የሚጥሰው ሳይሆን ቋሚ ዓለም አቀፍ ሕግ ነው። ወለጋ ላይ እየተገረሰሰ ያለው ይህ ዓለም አቀፍ ሕግ ነው! አንድ ጊዜ ብቻ አይደለም! መአት ጊዜ ነው!
የክልሉም የፌደራል መንግስትም ንፁሃን አማራዎች “ድረሱልን” ሲሉ እየደረሱ አይደለም። መፍትሄው አማራዎች ራሳቸውን እንዲከላከሉ ማድረግ ነው። ማስታጠቅ ነው።
የኦሮሚያ ክልል መንግስት በርካታ ፓርኮች አሉ። ፓርኮቹን በበርካታ ጠባቂ ያስጠብቃል። የዱር እንስሳትን የሚያስጠብቅ መንግስት ግን፣ አማራዎች ድረሱልኝ እያሉ ሲያልቁ ጥበቃ እያደረገ አይደለም። የዱር እንሰሳት “ድረሱልን” የሚሉ ቢሆን ኖሮ የክልሉም የፌደራል መንግስትም ሮጦ ይደርሳል። ንፁሃን አማራዎች ድረሱልን ሲሉ ግን የሚጨንቀው አልተገኘም። መፍትሔው ንፁሃን አማራዎች ራሳቸውን እንዲከላከሉ ማስታጠቅ ነው!
ትህነግና ኦነግ በይፋ ግንባር ፈጥረዋል። ትህነግ በይፋ የከፈተብን ግንባር ላይ ከተረባረብን በኦነግ በኩል የከፈተው ግንባር ላይ ለምንድን ነው የማንረባረበው? ትህነግም ንፁሃንን ይጨፈጭፋል፣ ኦነግም ንፁሃንን ይጨፈጭፋል። በይፋ የተከፈተ ጦርነት አይደበቅም። ንፁሃን አማራዎች ታጥቀው ራሳቸውን እንዲከላከሉ ከማድረግ በተጨማሪ ከኦሮሚያ ክልል ካልቻለ እንደ መተከሉ የሌሎች ክልሎች ልዩ ኃይሎችም መግባት አለባቸው።
ለፀረ ትህነግ ዘመቻው በአገር ደረጃ ወጣቶች እየሰለጠኑ ነው። የሁለት ሳምንትም የወርም ስልጠና እየወሰዱ ነው። ትህነግ በኦነግ በኩል ለከፈተው ዘመቻም የአካባቢው ወጣት በተለይ የሚጠቃው አማራና ነገ የሚጠቃው ሌላው ኢትዮጵያዊ መሰልጠን አለበት። የወለጋው ጭፍጨፋ የጦርነቱ አካል ነው! በንፁሃን ላይ ጦርነት ተከፍቶ ደግሞ ዝምታ አይመረጥም። እየተፈፀመ ያለው ጭፍጨፋ ነው። ድረሱልኝ እየተባለ፣ ጭፍጨፋ እየተካሄደ እንዴት ዝም ይባላል?
ከሶሻል ሚዲያ በመረጃ ኮም የተሰበሰቡ መረጃዎች ናቸው።