በአፋር ክልል በኩል ትንኮሳ የፈጸመው የአሸባሪው ህወሓት ቡድን ተደመሰሰ


የመረጃ ቲቪን 24/7 የሳተላይት ስርጭት በመደገፍ የኢትዮጵያ ህዝብ አማራጭ እና ትክክለኛ መረጃ በማግኘት እራሱን ከተጋረጠበት አደጋ መከላከል እንዲችል እናግዝ። በአሁኑ ወቅት ከመረጃ ቲቪ በስተቀር ሌሎች ሁሉም በኢትዮጵያ ያሉ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የመንግስት የፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ናቸው። ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ የከፈትነው የመረጃ ቲቪ የሳተላይት ስርጭት የአንድ ዓመት ወጪን ለመሸፈን ነው። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን ድጋፍዎትን ይለግሱ » https://gofund.me/54405070

የአሸባሪው ህወሓት ጁንታ “ሜይዴይ” በሚል ሰይሞ በአፋር ክልል አለሌ ሱሉላ በሚባል አካባቢ ያሰማራው ቡድን የሽብር ጥቃት በመፈጸሙ ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን የኢፌዴሪ አገር መከላከያ ሰራዊት አስታወቀ።

የኢፌዴሪ አገር መከላከያ ሰራዊት የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የአሸባሪው ህወሓት ጁንታ በቆቦም በተመሳሳይ የሽብር ቡድን አሰማርቶ ጥቃት ሰንዝሮ ነበር፡፡

ይሁን እንጂ የአገር መከላከያ ሠራዊት በወሰደው የመከላከል እርምጃ ቡድኑ መደምሰሱን እና ለውጊያ ያሰማራቸው በርካታ ህጻናት መማረካቸውን ኮሎኔል ጌትነት ተናግረዋል።

መንግስት ለትግራይ ህዝብ በማሰብ የወሰደውን የተናጠል የተኩስ አቁም እርምጃ አሸባሪው ሕወሓት የሽብር ተግባር ለመፈጸም እንደመልካም አጋጣሚ እንደወሰደው ጠቅሰው፤ ቡድኑ ደግሞ ትንኮሳ ከፈጸመ የመከላከል እርምጃው እንደሚወሰድበት አረጋግጠዋል።

የአሸባሪው ሕወሓት ጁንታ ትንኮሳ ያለማቆሙን በማየት ለአገር መከላከያ ሠራዊት መንግስት ትዕዛዝ ከሰጠ በቡድኑ ላይ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ ለማጥፋት ሠራዊቱ ዝግጁ መሆኑንም ኮሎኔል ጌትነት አስታውቀዋል።