ኢትዮጵያን ጨምሮ በስድስት ሃገራት የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሟል – የዩናይትድ ስቴትስ ውጪ ጉዳይ ሚኒስተር


የመረጃ ቲቪን 24/7 የሳተላይት ስርጭት በመደገፍ የኢትዮጵያ ህዝብ አማራጭ እና ትክክለኛ መረጃ በማግኘት እራሱን ከተጋረጠበት አደጋ መከላከል እንዲችል እናግዝ። በአሁኑ ወቅት ከመረጃ ቲቪ በስተቀር ሌሎች ሁሉም በኢትዮጵያ ያሉ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የመንግስት የፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ናቸው። ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ የከፈትነው የመረጃ ቲቪ የሳተላይት ስርጭት የአንድ ዓመት ወጪን ለመሸፈን ነው። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን ድጋፍዎትን ይለግሱ » https://gofund.me/54405070

VOA : የዩናይትድ ስቴትስ ውጪ ጉዳይ ሚኒስተር አንተኒ ብሊንከን ሰኞ ዕለት ዓመታዊ የዘር ማጥፋት እና የጭካኔ መከላከል ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን በሪፖርቱም ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሞባቸዋል የተባሉ ስድስት ተጠቅሰዋል፡፡ ሃገራቱም በርማ በመባል የምትታወቀው ማይናማር፣ ቻይና፣ ኢትዮጵያ ፣ ኢራቅ ሶሪያ እና ደቡብ ሱዳን ናቸው፡፡

ሚኒስተሩ በተጨማሪም ለውጥ ለማምጣት “በዲፕሎማሲ፣ በውጪ ሃገር እርዳታ፣ እውነታውን በማፈላለግ ተልዕኮ፣ በገንዘብ፣ በተሳትፎ ድጋፍ እና ይህን በመስሉ እጃቸን ላይ ባሉ የተቀናጀ ዓለም አቀፍ ተጽእኖ እና ምላሽ መስጠት የሚረዱ ሪፖርቶችን በማውጣትም ባለው ነገር ሁሉ እንጥራለን” ብለዋል፡፡