የኤርትራ ወታደሮች መቼ ከትግራይ ክልል ሙሉ በሙሉ ለቀው እንደሚወጡ መረጃው የለኝም – ዲና ሙፍቲ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


  • የኢትዮጵያ መንግስት ቀይ ባህር ላይ የጦር ቤዝ ሊገነባ ነው እይተባለ በአንዳንድ የግብጽ ሚዲያዎች የሚነዛው መረጃ የሃሰት መረጃ ነው
  • የኤርትራ ወታደሮች መቼ ከትግራይ ክልል ሙሉ በሙሉ ለቀው እንደሚወጡ መረጃው የለኝም ሲሉ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ።
  • የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል- አቀባይ ክቡር አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የሰጡት የፕሬስ መግለጫ፣

በትግራይ ክልል በነበረው ጦርነት ምክንያት በተፈጠረው ክፍተት ወደ ክልሉ ገብተው የነበሩት የኤርትራ ወታደሮች መውጣት መጀመራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሆኖም ሙሉ ለሙሉ ክልሉን ለቀው መቼ እንደሚወጡ በውል የተቆረጠ ቀን አለመቀመጡን አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናግረዋል፡፡

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ፣በጉዳዩ ላይ ከሰሞኑ ከመከላከያ ሃላፊዎች ጋር ውይይት መደረጉን አንስተው የኤርትራ ወታደሮች መውጣት መጀመራቸውን ከአመራሮቹ ሰምተናል ብለዋል ።

ይሁን እንጂ ወታደሮቹ መቼ ሙሉ በሙሉ ክልሉን ለቀው እንደሚወጡ መረጃው የለኝም ነው ያሉት አምባሳደር ዲና።

መንግስት ሕግ ማስከበር ባለው ዘመቻ ምክንያት ወደ ትግራይ ክልል የገቡት የኤርትራ ወታደሮች እንደሚወጡ የሁለቱ አገራት መሪዎች ስምምነት ላይ ስለመድረሳቸው መናገራቸው የሚታወስ ነው።

የኢትዮጵያ መንግስት ቀይ ባህር ላይ የጦር ቤዝ ሊገነባ ነው እይተባለ በአንዳንድ የግብጽ ሚዲያዎች የሚነዛው መረጃ የሃሰት መረጃ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በመግለጫቸው እንዳስታወቁት፤ የኢትዮጵያ መንግስት ቀይ ባህር ላይ የጦር ቤዝ ሊገነባ ነው እይተባለ በአንዳንድ የግብጽ ሚዲያዎች የሚነዛው መረጃ የሃሰት መረጃ ነው ብለዋል።
የተሳሳተ መረጃ በኢትዮጵያ ላይ ለምን እንደሚለቁ ይታወቃል ያሉት አምባሳደር ዲና፣ እነሱ የእራሳቸውን አጀንዳ ለማራመድ ስለሚፈልጉ ተመሳሳይ የሃሰት መረጃዎችን በኢትዮጵያ ላይ በማሰራጨት ላይ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡አምባሳደር ዲና እንዳስታወቁት፤ በትግራይ ክልል በዓለም አቀፍ ተቋማትና አንዳንድ የውጭ ሚዲያዎች የሚቀርበው ሪፖርት ከዕውነት የራቀና መሬት ላይ ያለውን እውነታ ያላገናዘበ ነው።
በክልሉ አንድ ነጥብ 2 ሚሊዮን አርሶ አደሮች ተጠቃሚ የሚሆኑበት ስራ እየተከናወነ ይገኛል ያሉት አምባሳደሩ 70 በመቶው የትግራይ የሚታረስ መሬት ለእርሻ ስራ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል፡፡ መንግስት አስፈላጊውን የሰብአዊ አቅርቦት እያከናወነ ባለበት ሁኔታ ችግሩ ወደረሃብ ይሸጋገራል የሚል ሪፖርት መቅረቡም ስህተት ነው ብለዋል አምባሳደሩ።
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል- አቀባይ ክቡር አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የሰጡት የፕሬስ መግለጫ፣
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል-አቀባይ ክቡር አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ፤ ሰኔ 03 ቀን 2013 ዓ.ም ለመገናኛ ብዙኃን ሳምንታዊ የፕሬስ መግለጫ ሰጥተዋል።
መግለጫው በፖለቲካ ዲፕሎማሲ፣፣ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ እንዲሁም የዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲን የተመለከቱ ሳምንታዊ ክንዋኔዎችን የዳስሰዋል።
1.ከፖለቲካ ዲፕሎማሲ አኳያ
• ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የለጋሽ አገሮች አምባሳደሮች እና የሰብአዊ ድጋፍ ሰጭ ድርጅቶች ተወካዮች በተገኙበት ፤ በትግራይ ክልል ህግ ማስከበር ዘመቻ ተከትሎ በተሰሩ ሥራዎችና ባጋጠሙ ችግሮች ዙሪያ በተዘጋጀው የምክከር መድረክ ላይ በተዛቡ መረጃዎች መነሻነት በመንግስት የተሰሩ ሥራዎችን ማንኳሰስ እና እውቅና መንፈግ በሞራል ፣በፖለቲካ እና በህግም ተቀባይነት የሌለው ተግባር መሆኑን ክቡር አቶ ደመቀ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። በመድረኩም ለ4.9 ሚሊዮን ዜጎች በመጀመሪያ ዙር እንዲሁም በሁለተኛ እና በ3ኛ ዙር በድምሩ ለ4.9 ሚሊዮች ዜጎች የሰብአዊ ዕርደታ መሰራጨቱ፣ 1.9 ሚሊዮን ተፈናቃዮችን መልሶ ለማቋቋም ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑ ፤46 ነጥብ 5 የጤና ተቋማት ወደ ስራ ማስገባት መቻሉ፣70 በመቶ የሚሆነዉ የእርሻ መሬት ለክረምት ወቅት ዝግጁ መሆኑ እና 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን የሚሆኑ አርሶ አደሮችን ለማሳተፍ ዝግት መደረጉን፣ የጨርቃ ጨርቅና የሲሚንቶ ፋብሪካዎችን ጨምሮ ሌሎች ፋብሪካዎችም ወደ ስራ እንዲገቡ መደረጉ፣የኤርትራ ጦር ከኢትዮጵያ እየወጣ መሆኑን ለተሳታፊዎቹ መገለጹን አብራርተዋል፡፡
• የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከኬንያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከክብርት ሪቼይል ኦማሞ ጋር በህዳሴ ግድብ፣በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ውዝግብ፣ በ6ኛው አገራዊ ምርጫ እንዲሁም በሁለቱ አገሮች መካከል የተፈረሙ ስምምነቶችን ተግባራዊ ማድረግ እና በሁለቱ አገሮች የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነትን በማሳደግ ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡
• በተያያዘም ክቡር የኬንያ ሪፐብሊክ ፕሪዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በአገራችን የይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገዋል። በወቅቱም ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ጋር በተለያዩ ቀጠናዊ እና የሁለትዮሽ ግንኙነቶች በተመለከተ ውይይት አድርገዋል። በተጓዳኝም በሳፋሪኮም የስምምነት ላይ ተገኝተው የፊርማ ስነ- ስርዓቱን ላይ መገኘታቸውን ተናግረዋል፡፡
• የውሃ ሃብት፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ የተመራ የልዑካን ቡድን በደቡብ ሱዳን ጉብኝት በማድረግ ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድን የጸላከን መልዕክት ለደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ለክቡር ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት አድርሰዋል። በሕዳሴ ግድብ ድርድር ሂደት፣ በኢትዮ-ሱዳን የድንበር ውዝግብ እንዲሁም በትግራይ ወቅታዊ ሁኔታና በቅርቡ በሚካሄደው አገራዊ ምርጫ ዙሪያ ለፕሬዝዳንቱ ፣ ውሃና መስኖ፣ ለኃይልና ግድቦች እንዲሁም የአከባቢና ደን ሚኒስትሮች ገለጻ ሰጥተዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ እና ሚኒስትሮች ኢትዮጵያ ውሃውን መጠቀም መብቷ እንደሆነ እና ከግድቡ ሃይል ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ጠቅሰው ፤ግድቡም ሆነ የድንበር ጉዳይ በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንዲፈታ የበኩላቸውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን መጥቀሳቸውን ገልጸዋል፡፡
በተለያዩ አገራት ተቀማጭ የሆኑ ሚስዮኖቻችን በወቅታዊ ጉዳይ፣በሁለትዮሽና በባለብዙ ወገን ጉዳዮች ዙሪያ
• በደቡብ ሱዳን ክቡር አምባሳደር ነቢል ማህዲ ከደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዝዳንት ከክብርት ሬቤካ ኒያንዴንግ ዲማቢዮር ጋር በሁለትዮሽና አካባቢያዊ ጉዳዮች በተለይም በሕዳሴ ግድብ ድርድር ሂደት፣ በኢትዮ-ሱዳን የድንበር ሁኔታ እንዲሁም በትግራይ ወቅታዊ ሁኔታና በቀጣዩ አገራዊ ምርጫ ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ምክትል ፕሬዝዳንቷ ከሱዳን በኩል የተፈጠረው ችግር እንዳሳዘናቸው ጠቅሰው ፤ደቡብ ሱዳን ችግሩ በውይይት እንዲፈታ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል ፡፡ ከግድቡ የሚመነጭ ኃይልም ተጠቃሚ እንደሚያደርቻው ተናግረዋል፡፡
• በጂቡቲ ክቡር አምባሳደር ብረሃኑ ፀጋዬ ከጂቡቲ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከክቡር መሃመድ አል ዩሱፍ ጋር ባደረጉት ውይይት የትግራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ፣በቀጣይ 6ኛው አገራዊ ምርጫ እና በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩም ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ግንኙነት በበርካታ መስኮች ለማስፋት ፍላጎታቸው መሆኑን መናገራቸውን ጠቅሰዋል፡፡
• በኡጋንዳ ክብርት አምባሳደር አለምፀሃይ መሰረት ከዩጋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ጋር በትግራይ ክልል መልሶ ማቋቋም እና ሰብአዊ እርዳታ እና 6ኛው አገራዊ ምርጫ አስመልክተው ውይይት አድርገዋል፡፡
• በእንግሊዝ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ መንግስት ረሃብን እንደ ጦር መሳሪያ እየተጠቀመ ነው በማለት እየቀረቡ ያሉ የሀሰት ክሶች አስመልከቶ መግለጫ ማውጣታቸውን ጠቅሰዋል፡፡
• ክቡር አምባሳደር ሀሰን ታጁ ለኢራቅ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት፣ ክቡር አምባሳደር ሚሊዮን ሳሙኤል ለኢስቶኒያ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት እና ክብርት አምባሳደር ደሚቱ ሀምቤሳ ለዓለም ምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር የሹመት ደብዳቤያቸውን አቅርበዋል፡፡
2.ኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ዘርፍ
2.1 ኢንቨስትመንትን በተመለከተ፣
• የጃፓኑ ሳሚቶም ኩባንያ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ውስጥ ከ2 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ በቴሌኮም ዘርፍ ኢንቨስት ለማድረግ ዕቅድ ያላው መሆኑን መጥቀሱ፣
• ሙምባይ የሚገኘው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት ከIndian Business Group (IBG) ጋር በመተባበር “Trade & Investment opportunities in Ethiopia” በሚል ርዕስ የበይነ- መረብ ውይይት ማካሄዳቸውን፣
• ቾንቺን የሚገኘው የአ.ፌ.ዲ.ሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት Ethio – Tongxing Investment Forum የተሰኘ ፎረም አዘጋጅቷል። በቾንቺን የሚገኙ ኩባንያዎች በአገራችን ኢንቨስት ለማድረግ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው መታወቁን፣
• ቾንቺን በሚገኘው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት የተመለመለ DIDI Chuxing Technology Co. Ltd የተባለ ኩባንያ በትራንስፖርት እና በሎጀስቲክ ዘርፍ ላይ የተሰማራ አለም ዓቀፍ ኩባንያ በአገራችን በትራንስፖርት ዘርፍ ላይ ለመሰማራት ፍላጎት በማሳየቱ የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖረው ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር በበይነ-መረብ ውይይት ማድረጋቸውን፣
• የአሜሪካ ተቋማት በኢትዮጵያ በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው መግለጻቸውን ገልጸዋል፡፡
2.2 ንግድን በተመለከተ፣
• የጓንጆ የኢፌዲሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት Blue Ocean Strategy ከተባለ የቢዝነስ ማስፋፊያ አማካሪ ድርጅትና ከሌሎች አካላት ጋር በመተባበር “Making Inroads to China for Ethiopian Exporters” በሚል ርዕስ ምርቶቻቸውን ለቻይና ገበያ የሚያቀርቡ የአገራችን ላኪዎችና ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በዌቢናር ተሰጥቷል፡፡
3.ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ዘርፍ፣
• በካናዳ የተቋቋመው የጥምረት ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የአልበርታ ቻፕተር (Alliance for GERD in Canada, Alberta chapter) በካናዳ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በመተባበር በአልበርታ ግዛት በካልጋሪ ከተማ፣ ኤድመንተን ከተማ፣ ሌትብሪጅና ፎርትማክመሪ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ-ኢትዮጵያዊያንን ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከ140,000 የካናዳ ዶላር በላይ ገቢ ሰብስበዋል፡፡
• በአሜሪካ የሚኔሶታ_ሚድዌስት የህዳሴ_ግድብ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ በ2ኛው ዙር 50,000 (ሃምሳ ሺህ) ዶላር ሰብስቦ ለቆንስል ጄኔራል ለአምባሳደር አብዱላዚዝ መሐመድ አስረክበዋል፡፡ ኮሚቴው ከዚህ ቀደም 40,000 (አርባ ሺህ) ዶላር ለግድቡ ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ በድምሩ 90,000(ዘጠና ሺህ) ለግድቡ የዳያስፖራ አባሉ ድጋፍ አድርጓል፡፡
• ከሳዑዲ አረቢያ አንድ ሺህ አንድ መቶ ሰላሳ ስድስት (1136) ዜጎቻችን ወደ ሀገር ቤት መመለሳቸውን ገልጸዋል ፡፡