የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ክልል ለሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት መሰናክል እየሆነ ነው – ሳማንታ ፓዎር


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በትግራይ ክልል የኢትዮጵያ መንግሥት ለሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት መሰናክል እየሆነ እንደሆነ የአሜሪካው የልማት ተራድዖ ድርጅት ዩኤስአይዲ ሃላፊ ሳማንታ ፓዎር በትዊተር ገጻቸው ገልጠዋል፡፡

በክልሉ 5.2 ሚሊዮን ዜጎች ምግብ ዕርዳታ እንደሚፈልጉ የጠቀሱት ሃላፊዋ፣ ሁኔታው ከቀውስ ደረጃ አልፏል ብለዋል፡፡ ነገ የአሜሪካ ዩኤስአይዲ እና የአውሮፓ ኅብረት የሰብዓዊ እና ልማት ዕርዳታ ሃላፊዎች በክልል ሰብዓዊ ሁኔታ በሚያደርጉት ውይይት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ዕርዳታን እንዳያሰናክልና ግጭት እንዲያቆም ጫና እንደሚያደርጉ ከወዲሁ አስታውቀዋል፡፡

Readout For Immediate Release – https://www.usaid.gov/news-information/press-releases/jun-9-2021-usaid-administrator-power-held-urgent-meetings-famine-atrocities-tigray