የሚያዚያ 27 80ኛ ዓመት የድል በዓል ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ አርበኞች እና የአዲስ አበባ ህዝብ በተገኘበት በአራት ኪሎ ይከበራል ተባለ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


EBC : የሀገር ጠላቶችን ለማሸነፍ ኢትዮጵያዊያን በአንድነት ሊቆሙ እንደሚገባቸው የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዝዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን አሳስበዋል።

ኢትዮጵያ ከ80 ዓመት በፊት የገጠማት የውጪ ወረራ የሚመሳሰል ችግር እየገጠማት መሆኑን ነው የማህበሩ ፕሬዝዳንት የገለፁት።

የማህበሩ ፕሬዝዳንት በመጪው እሮብ የሚከበረውን 80ኛ ዓመት የድል በዓል አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሀን መግለጫ ሰጥተዋል።

የሚያዚያ 27 የድል በዓል ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ አርበኞች እና የአዲስ አበባ ህዝብ በተገኘበት በአራት ኪሎ እንደሚከበር ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ጠላቶቿ በዘርና በሀይማኖት ሊከፋፍሏት በመጣደፍ በኃይል ሊያስፈራሩ እየሞከሩ ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ ጠላቶች ህዝቡና መሪዎች እንዳይተማመኑ ሴራ እየሰሩ እንደሆነም በመግለጫቸው አንስተዋል።

ሀያላን መንግስታት ሳይቀሩ ከግፈኞችና ከሀገር ጠላቶች ጎን ሲሆኑ የሀገር ውስጥ ባንዳዎችም ሀገር የማፍረስ ሴራው ደጋፊ ሲሆኑ ይታያል ነው ያሉት የማህበሩ ፕሬዝዳንት።

ኢትዮጵያ ከውስጥም ከውጪም ጠላቶቿ ቢተባበሩባትም ሊያቆስሏት ይችሉ ይሆናል እንጅ አያሸሸንፏትም ብለዋል ፕሬዝዳንቱ በመግለጫቸው።

ኢትዮጵያ በድል አድራጊነት ለህዝቦቿ ብቻ ሳይሆን ለመላው ጥቁር ህዝብና በቅኝ አገዛዝ ስር ለነበሩ ሁሉ ተስፋና ኩራት ሆና የቀጠለች መሆኗንም አንስተዋል።

በቀጣይም የህዳሴ ግድብን በማጠናቀቅ ኢትዮጵያ ጠላቶቿን ልታሳፍር እንደሚገባ በመግለጫቸው ላይ አንስተዋል።

ቀጣዩን የምርጫ ጊዜም ሰላማዊ በሆነ መንገድ በማከናወን ምርጫችን የሆነ መንግስት በመመስረት የሀገር ጠላቶችንና የውስጥ ቅጥረኞችን ወደ ጠርዝ ተገፍተው እንዲወድቁ ልናደርግ ይገባል ብለዋል።