በዓል ሰቆጣ ነኝ ያለው ሕወሓት በአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ ተሽመድምዶ ቀርቷል።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


May be an image of outdoors, tree and textዋግ ትግራይ ክልልን በ4 ወረዳዎች ያዋስናል። ይሄውም በወፍላ ወረዳ ፣ በዛታ ወረዳ ፣ በጻግብጅ ወረዳ እና በአበርገሌ ወረዳ። በዚህም ምክኒያት ህወሓት በተደጋጋሚ ዋግን በኮረም አሸንጌ ፣ በጻግብጅ ምን አለፋችሁ በዓራቱም ወረዳዎች ጥቃት ለማድረስ ሞክሯል። በአራቱም አቅጣጫ ንጹሐንን ገሏል ፣ እህል እና ለህክምና ማሳለጫ የማያገለግሉ አንቡላንሶችን ጭምር አቃጥሏል። ነገር ግን የሚዋጉትን የአማራ ክልል ልዩ ኃይልና ማሊሻ መቋቋም አልቻለም። በተደጋጋሚ ተመትቶ በሽንፈት ተመልሷል።
.
ሰሞኑን በአበርገሌ እንደ አሸባሪነት ባህሪው ተደብቆና ተመሳስሎ ጥቃት ለማድረስ ሲሞክር የአማራ ልዩ ኃይል ቅንድብ ቅንድቡን ብሎ ሲመልሰው ተበሳጭቶ በወሬ አቀባዮቹ በኩል በዓል ሰቆጣ ነኝ ብሎ ማስወራት ጀመረ። ነገር ግን እንኳን ሰቆጣ የዋግን የጫፍ ቀበሌ ማለፍ አቀበት ሆኖበት እንጉርጉሮ ላይ ነው። አሁን አሁንማ የህዝቡ ቁጣ ተጨምሮበት ድጋሚ ለማጥቃት የማይሞከር እየሆነ ነው።
.
በግራ ካሱ እና በዛታ መስመር ልዪ ኃይላችንና ሚሊሻችን የከፈለውን መስዋትነት ዘንግታችሁ ሰቆጣ ደሞዝ እየተቆረጠላችሁ ወፍላን በቸልታ አላፊ እንዲወስደው ዛሬም እንደትናንቱ የምትደሉቱ በፍጹም አንላቀቅም። ጥንትም አሁንም ወደፊትም ወፍላ ዋግ ናት። ከዚህ ውጭ ያለው ነገር በሙሉ ሰላም ሊፈጥር የማይችል መርዘኛ ተግባር ብቻ ነው። ወጣቱ ዝም ብሎ እየታዘበ ያለው አንዳንድ በዚህ ዙሪያ ስህተት ውስጥ ያሉ አመራሮች የሚስተካከሉ ከሆነ ብሎ ነው። የትግራይ ፖለቲከኞች ከዋግ ብሎም ከአማራ ክልል ጋር የሚኖራቸው ጉርብትና የሰመረና ሰላማዊ እንዲሆን ከፈለጉ ታሪክንና ማንነትን በወሬ ሳይሆን በተግባር ማክበር አለባቸው።

Sintayehu Eshetu