ለግድቡ ግንባታ ግብአት የሚያደርሱ 10 የከባድ መኪና ሹፌሮች በጉሙዝ ሽፍቶች ተገድለዋል።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የተሰራጨው መረጃ ሐሰት ነው – የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ሜጀር ጀነራል አስራት ዴኔሮ
ትናንት ማምሻውን በመተከል ዞን ጉባ ወረዳ ከህዳሴ ግድብ በ20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው ማንጎ ሰፈር ላይ ለግድቡ ግንባታ ግብአት የሚያደርሱ 10 የከባድ መኪና ሹፌሮች በጉሙዝ ሽፍቶች ተገድለዋል።
የንፁሃንን ሞትና መፈናቀል መታደግ ያቃተው የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት የአገሪቱን ቁጥር አንድ ፕሮጄክት የሆነው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ቀጠና በጉሙዝ ታጣቂዎች በቁጥጥር ስር እንዲሆን አድርጓል።
Journalist Yalelet Wondye
“…ፕሮጀክቱ ከማንኛውም የደህንነት ስጋት ነጻ ነው” – ሜ/ጄነራል አስራት ዴኔሮ

“ወደ ህዳሴው ግደቡ እቃ ጭነው ሲጓዙ የነበሩ 10 አሽከርካሪዎች ተገድለዋል ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ሐሰት ነው” ሲሉ የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ሜጀር ጀነራል አስራት ዴኔሮ ለአል ዐአይን አማርኛ ተናግሩ።

ጄነራሉ ፥ “በትናንትናው ዕለት ከ70 በላይ አሽከርካሪዎች ወደ ህዳሴው ግድብ የተለያዩ እቃዎችን እና ማሽነሪዎችን” ያለምንም ችግር አድርሰዋል ብለዋል፡፡

ለግድቡ እቃዎችን እና ማሽኖችን በማጓጓዝ ላይ ነበሩ 10 አሽከርካሪዎች በመተከል ዞን ማንጎ ከተማ ላይ በታጣቂዎች ተገደሉ የሚሉ መረጃዎች በተለይ በማህበራዊ ሚዲያዎች በመሰራጨት ከዛሬ ጠዋት ጀመሮ ሲሰራጭ ቆይቷል፡፡

ጀነራሉ አክለው፥ “ወደ ካማሼ በመምጣት ላይ ያለ አንድ አይሱዙ በታጣቂዎች ተተኩሶበት ሹፌሩን ጨምሮ 3 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ በአካባቢው ያለው የጸጥታ ሀይል የከፋ ጉዳት ሳይደርስ ሁኔታውን ተቆጣጥሮታል” ሲሉ ተናግረዋል።

ታላቁ የህዳሴው ግድብ 24 ሰዓት ክትትል እና ጥበቃ የሚደረግለት ብሔራዊ ፕሮጀክት ነው ያሉት ሌተናል ጀነራል አስራት ፕሮጀክቱ ከማንኛውም የደህንነት ስጋት ነጻ መሆኑንም ተናግረዋል።