ጅቡቲ የወቅቱ ትኩሳት ተጠቅማ እውን ግዛቷን እስከ አዋሽ ማዝለቅ ትፈልጋለች ?


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በብዙ ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ቅሬታ የፈጠረው የጂቡቲ ፕሬዝደንት የትዊተር ጽሁፍ “ባልተገባ መንገድ ተተርጉሟል” ተባለ

ፕሬዝደንቱ በትዊተር አድራሻቸው ያሰፈሩትን ጽሁፍ ከተወሰነ ቆይታ በኋላ አጥፍተዋል

አል-ዐይን

ኢስማኤል ኦማር ጊሌ-የጂቡቲ ፕሬዝደንት

“የፕሬዝደንቱ ሀሳብ ፈረንሳይኛው ችግር የለበትም ችግሩ የተፈጠረው በጎግል ወደ እንግሊዝኛ ሲቀየር ነው” -በኢትዮጵያ የጂቡቲ አምባሳደር

የጂቡቲው ፕሬዝደንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ ባሳለፍነው ቅዳሜ በፈረንሳይኛ ቋንቋ ለተከታዮቻቸው ስለ ‘አዋሽ ውሃ’ በትዊተር ገጻቸው ላይ ትዊት አደርገው ነበር።

ይህ የፕሬዝደንቱ ሀሳብ በጎግል መተርጎሚያ መሰረት ወደ እንግሊዘኛ ሲተረጎም “ጅቡቲ ለዜጎቿ ከአዋሽ ወንዝ ለማድረስ ትግሏን ትቀጥላለች” የሚል ሀሳብ ያዘለ ነው።

የፕሬዝደንቱ የፈረንሳይኛ ቀጥተኛ ትርጉም ደግሞ “ከአሁን በኋላ ትኩረታችንን ፣ ለዜጎቻችን የንጹህ የመጠጥ ውሃ እጅግ ጠቃሚ ከሆነው ከአዋሽ ወንዝ ማግኘቱ ላይ እናደርጋለን፤ ጉዳዩ በአካባቢው ዋነኛው ፈተና ቢሆንም ችግሩን መፍታት እንፈልጋለን” ይላል፡፡

ፕሬዝደንቱ በትዊተር አድራሻቸው ያሰፈሩትን ጽሁፍ ፣ ተቃውሞ ሲበዛባቸው ፣ ከተወሰነ ቆይታ በኋላ አጥፍተዋል፡፡

ይሁንና አዋሽ የኢትዮጵያ ወንዝ ከመሆኑ በተጨማሪ ከኢትዮጵያ ውጭ እንደማይፈስ እየታወቀ ጂቡቲ ስለምን ይሄንን ልትል ቻለች? የሚለው ሀሳብ በብዙ ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ቅሬታን ፈጥሯል።

ብዙዎችም ከወቅቱ የፖለቲካ እና የዲፕሎማሲ ትኩሳት ተነስተው ጂቡቲም ልታጠቃን ትፈልጋለች ማለት ነው? የሚሉ የስጋት ሀሳቦችን አንስተዋል።

አል ዐይን አማርኛ በፕሬዝደንቱ የትዊተር ጽሁፍ ጉዳይ በኢትዮጵያ የጂቡቲ አምባሳደር መሀመድ ኢድሪስን ጠይቋል።

አምባሳደሩ አንዳሉት “ፕሬዝደንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ ትዊት ያደረጉት ሀሳብ ፈረንሳይኛው ችግር የለበትም ፤ ችግሩ የተፈጠረው በጎግል ትርጉም ወደ እንግሊዝኛ ሲቀየር ነው” ብለዋል።

“ኢትዮጵያ እና ጂቡቲ መቼም የማይናወጥ ወዳጅነት ያላቸው ሀገራት ናቸው” ያሉት አምባሳደሩ ፣ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ንጹህ የመጠጥ ውሃ እያገኘች መሆኑን ተናግረዋል።

“ጂቡቲ በፍጹም በአዋሽ ወንዝ ጉዳይ ፍላጎትም ይሁን ጥያቄ የላትም ፤ ከኢትዮጵያ ጋር ያለን ወዳጅነት ጽኑ እና ለአፍሪካዊያን ምሳሌ የሚሆን ነው”ም ብለዋል አምባሳደር መሀመድ።

ጂቡቲ በኢትዮጵያ በ330 ሚሊዮን ዶላር በራሷ ወጪ 220 ኪሎ ሜትር የሚረዝም የውሃ ማስተላለፊያ መስመር በመገንባት ከፈረንጆቹ 2019 አንስቶ 900 ሺህ ለሚሆኑ ዜጎቿ በነጻ ንጹህ የመጠጥ ውሃ በማግኘት ላይ ትገኛለች።