የአንጋፋው ድምፃዊ እና የዜማና ግጥም ደራሲ አየለ ማሞ የቀብር ስነስርዓት ተፈፀመ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የአንጋፋው ድምፃዊ እና የዜማና ግጥም ደራሲ አየለ ማሞ የቀብር ስነስርዓት ተፈፀመ፡፡
የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ዛሬ ቤተሰቦቹ፣ ዘመድ አዝማዶቹ ፣ የሙያ አጋሮቹ እንዲሁም አድናቂዎቹ በተገኙበት በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ተፈፅሟል፡፡
አርቲስት አየለ ማሞ ከዜማና ግጥም ደራሲነቱ ባለፈም የማንዶሊኑ ንጉስ በመባል ይታወቃል፡፡
አርቲስት አየለ ለአንጋፋ ድምጻውያን በርካታ ዜማዎችን ሰርቶ ከመስጠት ባለፈ ወይ ካሊፕሶ በሚለው ሙዚቃ በህዝብ ዘንድ ይበልጥ እውቅናን አግኝቷል፡፡
እንዲሁም በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውስጥ ከ1950ዎቹ ጀምሮ የበኩሉን አስተዋጽኦ ያበረከተ አንጋፋ ባለሙያም ነበር፡፡