በኦሮሚያ ክልል የሚደርሰዉ ጥቃትና ግጭት መንስኤ የፖለቲካ ጽንፈኝነትና መንግስት ለችግሩ ብዙ ትኩረት አለመስጠቱ ነው


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አከባቢዎች የሚደርሰዉ ጥቃትና ግጭት መንስኤ የፖለቲካ ጽንፈኝነት እና መንግስት ለችግሩ ብዙ ትኩረት አለመስጠቱ እንደሆነ ተቃዋሚዉ የኦሮሞ ፌዴራዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ) አስታወቀ፡፡የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ እንደሚሉት ችግሩ ለዘላቂዉ የሚፈታዉ መንግስት ሁሉንም ወገን ያሳተፈ ውይይት ሲያስተናግድ ብቻ ነው።የገዢዉ የብልፅግና ፓርቲ የዴሞክራሲ ማዕከል አስተባባሪ ቢቂላ ሁሪሳ ግን «የአፍራሽነት ሚና» ያላቸዉ ያሏቸውን የፖለቲካ ድርጅቶች በጥፋተኝነት ከሰዋል፡፡ DW