የጁንታው ርዝራዦች ወጣቶችን እያስገደዱ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ሰላምን እያደፈረሱ ነው – ሜ/ጀ መሐመድ ተሰማ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


“የጁንታው ርዝራዦችን ወደ ሕግ የማቅረብ ሥራው ተጠናክሮ እየቀጠለ ነው”፡- ሜ/ጀ መሐመድ ተሰማ
May be an image of 2 people, people standing and indoorበሰሜን እዝ ላይ ጁንታው ያደረሰውን ጥቃት ተከትሎ የተወሰደው የሕግ ማስከበር እርምጃ ቢጠናቀቅም ርዝራዦችን ወደ ሕግ የማቅረብ ሥራው ተጠናክሮ እንደቀጠለ የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜ/ጀ መሐመድ ተሰማ ገልጸዋል። ሜ/ጀ መሐመድ ተሰማ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን አሁናዊ ሁኔታ አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።
በሕግ የሚፈለጉ የጁንታው አባላት ሐሰተኛ መረጃዎችን በተለያዩ የሀገር ውስጥ እና በውጭ መገናኛ ብዙኃን በማድረስ ኅብረተሰቡን እያወዛገቡ መሆኑንም ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።ቡድኑ ቢደመሰስም ርዝራዦቹ ወጣቶችን እያስገደዱ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ሰላምን እያደፈረሱ ነው ሲሉም ተናግረዋል። እነዚህ ርዝራዦቹ ንፁሃን ዜጎችን ራሳቸው እየገደሉ መከላከያ ሠራዊት ጥቃት እንደፈፀመ ለማስመሰል የሚነዙት ፕሮፓጋንዳ መቀጠሉን እና ዓለም አቀፉን መገናኛ ብዙኃን እያደናገሩ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
በመሆኑንም በእነዚህ አካላት ላይ መከላከያው እርምጃ እየወሰደ እንደሚገኝ ገልጸዋል። የትግራይ ሕዝብ ለመከላከያ ሠራዊቱ እስካሁን ሲያደርግ የነበረውን ድጋፍ አሁንም አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።