ትግራይ ክልል ህወሓትን ከልቡ የሚጠየፍ ጠንካራ አመራር ያስፈልገዋል !


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ዶ/ር ሙሉ ነጋ ከኃላፊነታቸው እንደተነሱ እየተነገረ ነው ። መነሳታቸው ተገቢ ነው ።

መነሳታቸውም አይቀሬ ነው ። ክልሉ ግን ህወሓት ከልቡ የሚጠየፍ ጠንካራ አመራር ያስፈልገዋል ።

ምርጫ ደርሶ ህዝቡ የመሰለውን እስኪመርጥ ኮስተር ያለ ንፁህ አመራር ያስፈልገዋል ።

ትግራይ ውስጥ ብልፅግናን ተክሎ አሻንጉሊት አስተዳደር ለመትከል የሚደረገውን ፍላጎት እና ጥድፊያ ብትረሱት መልካም ውጤት ያመጣል ።

ከኮማንድ ፖስቱ ጋር እየተናበበ ህወሓትን ረስቶ ለህዝብ ከህዝብ ጎን የሆነ አመራር ነበር የሚያስፈልገው ።

አሁንም ጀሮ ብትሰጡ መልካም ነው ። ግዜው አላለፈም ። አቶ ተክሌ በቀለ ( ፖለቲከኛ የኢዜማ አመራር)