መተከል በድባጢ ወረዳ በርካታ ቤቶች መቃጠላቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


DW  : የቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች በሰው እና ንብረት አሁንም ጥቃቶች እየደረሱ መሆንን ነዋሪዎች አስታውቀዋል። በአካባቢው የሚስተዋለውን የጸጥታ ችግር መንግሥት በዘላቂነት እንዲፈታም ጠይቀዋል። በድባጢ ወረዳም ሰሙኑን በርካታ ቤቶች መቃጠላቸውን ነዋሪዎች የተናገሩ ሲሆን የመጓጓዣ አገልግሎት ባለመኖሩ መቸገራውንም አክለዋል። ከነዋሪው ለተነሱት ቅሬታዎች ከአካባቢው አስቸኳይ ጊዜ አስተዳደር ወይም ኮማንድ ፖስት ስልክ ባለማንሳታቸው መረጃ ለማግኘት አልተቻለም።