አስመራ – አዲስ አበባ / አስመራ – ዱባይ በረራ ሊጀመር ነው።
የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል በትዊተር ገፃቸው እንዳስታወቁት የትራንስፖርት እና ኮሙዩኒኬሽን ሚኒስቴር ጠቀሰው ሚያዝያ አጋማሽ ላይ የንግድ በረራዎችን በከፊል ይጀምራል ብለዋል። አቶ የማነ አያይዘውም የኮቪድ 19 ምርመራዎችን በጥንቃቄ በማድረግ ጠንካራ የሆኑ የመከላከያ ምርመራ እርምጃዎችን አካቶ በመተግበር ለአስመራ – አዲስ አበባ / አስመራ – ዱባይ መንገዶች ሳምንታዊ በረራዎች ይካሔዳሉ ሲል ገልጸዋል።
#Eritrea: Ministry of Transport & Communications announced today partial resumption of commercial flights in mid April. This will be confined to weekly flights for Asmara-Addis Abeba/Asmara-Dubai routes with implementation of rigorous preventive measures – prior PCR testing etc. pic.twitter.com/fGL7zlqsix
— Yemane G. Meskel (@hawelti) April 5, 2021