የኮንትሮባንዲስቶች ተባባሪ የሆኑ የጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞችና የፌደራል ፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ፡፡


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የጉምሩክ ኮሚሽን የኮሚሽኑ ሰራተኞችንና የፌደራል ፖሊስ አባላትን በቁጥጥር ስር አዋለ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጉምሩክ ኮሚሽን ከፌደራል ፖሊስ ጋር በመተባበር ከ3 ወር በላይ የፈጀ የኦፕሬሽን ስራ በመስራት የኮንቶሮባንድ እቃዎች፣ኮንትሮባዲስቶችንና ተባባሪዎቻቸውን በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ፡፡
በጉዳዩ ዙሪያ የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቀበታ በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
ኮንትሮባዲስቱ በአዋሽ መቆጣጠሪያ ጣቢያ የፌደራል ፖሊስ ሀላፊ የሻለቃ አዛዥ የሆነ ግለሰብን በጥቅም በመደለልና ከፌደራል ፖሊስ አባላትና እና ከአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሁለት ሁለት ሰዎችን መልምሎ እንዲያሰማራ በመመሳጠር የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቀላሉ ለማሳለፍ እየሰራ መሆኑን ጥቆማ የደረሰው የጉምሩክ ኮሚሽን ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ የኦፕሪሽን ስራ ለ3 ወር በመስራት መጋቢት 23 /2013 ዓም የኮንትሮባንድ እቃዎቹ፣ ኮንትሮባንዲስቶች እና ተባባሪዎቻቸው ጭምር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን በመግለጫው አንስተዋል፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽን
No photo description available.