“…የእጩ ተወዳዳሪዬ ቤት በጥይት ተደብድቧል” – የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


“…የእጩ ተወዳዳሪዬ ቤት በጥይት ተደብድቧል” – የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት

የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ጊዜ ሰሌዳ እንደሚያሳየው ዛሬ የእጩዎች ምዝገባ ተጠናቋል።

መኢአድ በዘንድሮው ምርጫ በፌዴራል ደረጃ መንግስት ለመስረት በሚስችል የምክር ቤት ወንበር ቁጥር እንደሚወዳደር እና እጩዎችንም በዚህ ደረጃ ማስመዝገቡን አሳውቋል።

መኢአድ በእጩ ማስመዝገብ ሂደቱ በጎንደር የአንድ እጩ ተወዳዳሪው ቤት በጥይት መደብደቡ የገጠመው ከፍተኛው ችግር እንደሆነ ገልጿል። በሌላ በኩል ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ላይ እጩ ተወዳዳሪው ማስፈራሪያና ዛቻ እንደደረሰበት አሳውቋል።

ምንም እንኳን ችግሮች ቢኖሩም ሂደቱ ጥሩ የሚባል እንደነበር ገልጿል።

ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ትናንት እንዳስታወቀዉ እስከ ትናንት ድረስ በምርጫዉ ለመወዳደር ምልክት ከፀደቀላቸው 53 የፖለቲካ ድርጅቶች ዕጩ ያስመዘገቡት 15ቱ ብቻ ናቸው።

መረጃው የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ነው።