የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ኢዜማ “ብርሃን” እንጂ “አምፖል ይዞ” ወደ ምርጫው አልመጣም – ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
“ብርሃን የሚገኘው በአምፖል ነው”- ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ለዚህ የሚሆን መልስ ያዘጋጁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “ብርሃን የሚገኘው በአምፖል ነው” ሲሉ የጭዳ-ጅማ የመንገድ ግንባታን ባስጀመሩበት መረሃ-ግብር ላይ ገልጸዋል፡፡ ጅማ እና አካባቢው ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ስፍራዎች አንደኛው ቢሆንም ባለፉት 30 ዓመታት መንግሥት ትኩረት ሳይሰጠው በመቆየቱ ፈጣን ለውጥ ማምጣት ተስኖት ነበር ብለዋል፡፡
–

ፕሮፌሰር ብርሃኑ በመርሃ ግብሩ ላይ ባሰሙት ንግግር፥ ገዢው ፓርቲ ከመጪው ምርጫ ጋር በተገናኘ “ግልጽ አቋሙን ሊያሳውቅባቸው ይገባል” ያሏቸውን ነጥቦች አንስተዋል።“ብልጽግና ፓርቲ የህወሓት እና የኢህአዴግ ወራሽ ሳይሆን ከሁለቱ የተለየ ፓርቲ መሆኑን በተግባር እንዲያሳየን እንሻለን” ብለዋል በንግግራቸው።የኢዜማው መሪ፤ መጪው ምርጫ ከዚህ ቀደም ከተካሄዱት አምስት ጠቅላላ ምርጫዎች የተለየ መሆኑን በንግግራቸው ጠቅሰዋል።

–
የኢዜማው መሪ“ኢህአዴግ ይባል የነበረው ድርጅት ስልጣን ከያዘ ወዲህ ምርጫ መሰል ነገሮች ሁሉ ተቆጥረው ስድስተኛ ይባል እንጂ፤ የእኛ ተስፋ ይህ ምርጫ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ነው” ሲሉ ለአሁኑ ምርጫ ያላቸውን ከፍተኛ ግምት ተናግረዋል። “ታሪክ በእኛ ላይ የጣለው ሃላፊነት ይህ ምርጫ ከዚህ በፊት እንደነበሩት የይስሙላ ወይም የሙከራ ሳይሆን፤ በእርግጥም የመጀመሪያ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ማድረግ ነው” ሲሉም አክለዋል።
–
