የአክሲዮን ገበያ ማቋቋም ጥያቄ የማይነሳበትና ወቅቱ የሚጠይቀው ወሳኝ አገራዊ ጉዳይ ነው – አቶ ኤርሚያስ አመልጋ

‹‹የአክሲዮን ገበያ ማቋቋም ጥያቄ የማይነሳበትና ወቅቱ የሚጠይቀው ወሳኝ አገራዊ ጉዳይ ነው›› አቶ ኤርሚያስ አመልጋ፣ የፋይናንስና የኢኮኖሚ ባለሙያ

ሪፖርተር  – በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በአፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት እ.ኤ.አ. በ1956 የተመሠረተው የአዲስ አበባ የአክሲዮን ንግድ ማኅበር፣ በአፍሪካ ሁለተኛው እንደነበር ይገነገርለታል፡፡ በብሔራዊ ባንክ አደራጅነት የተመሠረተው ‹‹የአዲስ አበባ ሼር ዲሊንግ ግሩፕ›› በወቅቱ አገር በቀል የነበሩ የአክሲዮን ኩባንያዎች የአክሲዮን ይዞታቸውን በስፋት የሚሸጡበት ማዕከል ከመፍጠር በተጨማሪ፣ የተለያዩ የአክሲዮን ንግድን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ሕጎችንና ደረጃዎችን ማጎልበት መቻሉ ይነገራል፡፡

የደርግ መንግሥት ወደ ሥልጣን ከመምጣቱና አብዛኛው የግል ዘርፍ ተዋናዮች ከመክሰማቸው በፊት፣ በኢትዮጵያ ግንባር ቀደም የሚባሉ ኩባንያዎች ሳይቀሩ ባለአክሲዮን እንደነበሩ ይወሳል፡፡ በተለይ እንደ አዲስ አበባ ባንክ፣ የኢትዮጵያ ቄራዎች ድርጀት፣ ጠርሙስ ፋብሪካ፣ ኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅ ኩባንያ፣ ኤችቪኤ ኢትዮጵያ፣ ተንዳሆ እርሻና ሌሎች እ.ኤ.አ. ከ1960 እስከ 1974 ባለው ጊዜ ውስጥ አክሲዮን የሸጡ ኩባንያዎች እንደነበሩ ይነገራል፡፡ በደርግ ዘመን ፈርሶ በኢሕአዴግ ዘመን ችላ ተብሎ ቆይቶ፣ በቅርቡ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ኢትዮጵያ የአክሲዮን ገበያ እንድታደራጅ ተወስኗል፡፡ የፋይናንስና የኢኮኖሚ ባለሙያው አቶ ኤርሚያስ አመልጋ ደግሞ፣ ከዓመታት በፊት የአክሲዮን ገበያ ለማደራጀት ከተነሱ ሰዎች መካከል በግንባር ቀደምትነት ስማቸው ይነሳል፡፡

የአክሰስ ካፒታል ኩባንያን በማቋቋምና በመምራት፣ እንዲሁም በርካታ አዳዲስ የኢንቨስትመንት ሐሳቦችን በኢትዮጵያ ተግባራዊ በማድረግ፣ እንዲሁምፋይናንስ ኢንዲስትሪው ውስጥ ባለአንድ ቅርንጫፍ ሆኖ የተመሠረተውን ዘመን ባንክን ያደራጁ በመሆናቸውም ይታወቃሉ፡፡ አቶ ኤርሚያስ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ (አሁን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ) ለአንድ ዓመት ከተማሩ በኋላ ወደ አሜሪካ ካቀኑ በኋላ ትምህርታቸውን በመቀጠል ኑሯቸውን እዚያው መሥርተው ቆይተዋል፡፡ አሜሪካ ዎልስትሪት የካፒታል ገበያ ውስጥ በመሥራት ልምድ ካካበቱ በኋላ የዛሬ 24 ዓመት ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት፣ ይህንኑ ልምድና ዕውቀታቸውን ይዘው በልዩ ልዩኢንቨስትመንት መስኮች ለመሰማራት ነበር፡፡ በዚህ ሒደትም በርካታ ውጣ ውረዶች ገጥመዋቸዋል፡፡ በቅርቡ በመንግሥት ውሳኔ እንዲመሠረት ይሁንታ ባገኘው አክሲዮን ገበያና ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ አቶ ኤርሚያስ ከሪፖርተር ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ እንዲህ ተጠናቅሯል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ: https://bit.ly/3bAeWRK