መተከል ዞን የሰዎች ህይወት እያለፈ፥ንብረትም እየወደመ ጥቃት አሁንም ቀጥሏል።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል ዞን ጥቃት አሁንም ቀጥሏል። የሰዎች ህይወት እያለፈ ነው፥ንብረትም እየወደመ ነው።

• አዲስ ማለዳ ጋዜጣ ታኅሳስ 26 በጭላንቆ ቀበሌ 7 ንፁሃን ዜጎች እና 4 የመከላከያ አባላት ለቡለን ወረዳ አጎራባች ከሆነው ካማሺ ዞን ያሶ ወረዳ የገቡ የታጠቁ ኃይሎች በከፈቱት ተኩስ መገደላቸውን በቅዳሜው እትሙ አስነብቧል።

• በወምበራ ወረዳ በጎንዲ በተባለ ቦታ ባለፈው ሳምንት ሀሙስ የጸጥታ ሀይሎችን ጨምሮ በግብርና ስራ ላይ የተሰማሩ 16 ሰዎች በተፈፀመባቸው ጥቃት ተገድለዋል። በንብረት ላይም ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።

• ጉባ ወረዳ ትናንት በደረሰ ጥቃት 11 ሰዎች ተገድለዋል።

• ትላንት ለሊት ድባጤ ወረዳ ‘ቆርቃ ቀበሌ’ በታጣቂዎች በተከፈተ ጥቃት ከ60 በላይ ንፁሃን መገደላቸውን የአይን እማኞች እና ከጥቃቱ ያመለጡ ሰዎችን ዋቢ አድርጎ ቪኦኤ ዘግቧል።

ከ25 በላይ ሰዎች ቆስለዋል፣ እጅግ ከፍተኛ ንብረት እንደወደመ ተነገሯል።

ቪኦኤ ሬድዮ ፥አንድ የአካባቢው የኮማንድ ፖስት አባል ጥቃቱ መፈፀሙን አረጋግጠዋል ብሏል። ነገር ግን የደረሰውን ጉዳት መጠን አልገለፁም፤አላረጋገጡም፣ መረጃም አልሰጡም።

የአካባቢው የቲክቫህ አባላት በተፈፀመው ጥቃት የሟቾች ቁጥር ከመቶ በላይ ነው ብለዋል።

• ትላንት እንዲሁም ዛሬ ከቻግኒ ወደ ግልገል በለስ በሚሄዱ መኪናዎች ላይ ጥቃት ተፈፅሞ ሁለት ሰው ሲገደል ሌሎች ቆስለዋል። ትላንት 1 ሰው ዛሬ 1 ሰው ተገድሏል።

አጠቃላይ ከላይ የተሰባሰቡት መረጃዎች የአይን እማኞችና ነዋሪዎች የሰጧቸው ሲሆኑ በመንግስት በኩል የተብራራ ዝርዝር መረጃ እስካሁን አልተሰጠም።

አሁንም አካባቢው ከፍተኛ የስጋት ቀጠና መሆኑን ነዋሪዎች እየገለፁ ነው።

ምንጭ፦ቢቢሲ፣ቪኦኤ፣አዲስማለዳ፣ዶቼ ቨለ