የንጹሐን ዜጎች በታጠቁ ኃይሎች መገደል አሁንም እንደቀጠለ ነው

በመተከል ዞን ለወራት በዘለቀው የንጹሐን ዜጎች በታጠቁ ኃይሎች መገደል አሁንም እንደቀጠለ መሆኑን አዲስ ማለዳ አገኘውት ያለው መረጃ ያሳያል።

ባሳለፍነው ታኅሳስ 26/2013 አራት የመከላከያ አባላትና ሰባት የማኅበረሰብ ክፍሎች ለቡለን ወረዳ አጎራባች ከሆነው ካማሺ ዞን ያሶ ወረዳ የገቡ የታጠቁ ኃይሎች በከፈቱት ተኩስ ተገለዋል።

በዞኑ ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ኃይሎች ጥቃት እንደቀድሞው ባይሆንም ሰዎች በጫካ መገደላቸው አለመቆሙን ዘገባው ያመለክታል። በቡለን ወረዳ ቢሸኖ ቀበሌ ሰብል በመሰብሰብ ላይ እያሉ ኹለት ግለሰቦች በጥይት ተመተው መቁሰላቸውን አንደ አንድ ማሳያ ይጠቅሳል።

የቡለን ወረዳ ወጣቶች በጎፈቃደኛ ማኅበር አባላት ለአዲስ ማለዳ እንደገለጹት በማቆያ ማዕከላት የምግብና አልባሳት ድጋፍ እቀረበ ቢሆንም የጤና አገልግሎት ክፍተት ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አሕመድ የተቋቋመው አዲሱ የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት ግብረ ኃይል እስካሁን በሰራቸው ሥራዎች አንጻራዊ መሻሻሎችን ማምጣቱን አዲስ ማለዳ በዘገባው አካቷል።