በደቡብ ክልል ኮንሶ ዳግም ግጭት ማገርሸቱ ተሰማ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ

በኮንሶ ዞን ሰገን ዙሪያ ወረዳ ዳግም ባገረሸ ግጭት ጉዳት መድረሱን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ።

በኮንሶ ዞን የሰላምና እርቅ ኮሚቴ ሰብሳቢ በደቡብ ክልል የፌዴራል መንግስት የክልል አወቃቀር የሰላም አምባሳደር አባል የባላባት ካላ ገዛኸኝ፥ ጥቃት አድራሾቹ ሰገን ዙሪያ ወረዳ ውስጥ ገብተው (መልካና ዱካያ፣ ሰገን ገነት፣ አዲስ ገበሬ፣ ገርጬ፣) ባሉት 9 ቀበሌዎች ውስጥ ሲያጠቁ ነበር ብለዋል።

ጥቃት አድራሾቹ ቤቶችን እያቃጠሉ፣ ሰው እየገደሉ ነው ያሉት ሲሉ ገልፀዋል።

በቾ፣ አዲስ ገበሬ፣ መለጋና ዱካያ፣ ገርጬ፣ ሰገን ገነት፣ ሉልቱ፣ ሌሎችም ቦታዎች ላይ ከፍተኛ ጥቃት መፈፀሙን አስረድተዋል።

ካሉት 9 ቀበሌዎች ጥቃት ያልደረሰበት ብርብርሳ ብቻ ሳይሆን አይቀርምም ብለዋል።

ከዚህ ቀደም በዞኑ ውስጥ ያሉ ሌሎች ወረዳዎች እርቀ ሰላም ለማውረድ ቢሞከርም ለውይይት ፍቃደኛ ያልሆኑ አካላት መኖራቸው መሰናክል ሆኗል ብለዋል።

በተደጋጋሚ የሚያገረሸው ግጭት ዋነኛው መንስኤ “ልዩ ወረዳ” የመሆን ጥያቄ እንደሆነ ገልፀዋል።

የኮንሶ ዞን ከሰገን አካባቢ ህዝቦች ዞን ወጥቶ ለብቻው ከተደራጀ በኃላ የመዋቅር እና የአስተዳደር ጥያቄ አለን የሚሉ አሉ።

በመዋቅር እና አስተዳደር ጥያቄ ምክንያት በአካባቢው በተደጋጋሚ ግጭቶች ይከሰታሉ፣ ያገረሻሉ።

በዚሁ አካባቢ ከዚህ ቀደም በተቀሰቀሰ ግጭት የሰዎች ህይወት አልፏል፥ ከ70 ሺህ በላይ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል። ~ ቢቢሲ