በመተከል በንፁሀን ላይ ጥቃቱ መቀጠሉ ተሰምቷል ።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ

የመተከል ጉዳይ ችግሩ ተራራ መፍትሄው ጠጠር ሆኗል።

መተከል፣ ማንዱራ፣ ኤዲዳ ቁጥር (2) የተፈፀመ ጥቃት።
( አሻራ )

የጉሙዝ አማፂ ቡድኑ ማንዱራ ወረዳ ኤዲዳ ቀበሌ/ቁጥር 2/ ላይ ዛሬም በህዝብ ማመላለሻ መኪና ላይ ጥቃት ፈፅሟል:: በጥቃቱም የአንድ ሰው ህይወት ያለፈ ሲሆን በርካቶች ቆስለዋል::ከ4ቀን በፊትም በዚሁ አካባቢ በተደረገ ጥቃት ሁለት(2)ሰዎች መገደላቸው እና አንድ ሰው መቁሰሉ ይታወቃል።

በመተከል እየተንቀሳቀሰ ያለው የቤጉህዴን፣ የቤህነን እና የኦነግ አማፂ ቡድን በጎሬላ ጦርነት እየተንቀሳቀሰ ነው:: ጉባ ላይ ዛሬም ጥቃት ፈፅሟል:: በድባጤ ፓርዘይትና ሳስ ቀበሌዋች ላይ ከአንድ ቀን በፊት ጥቃት መፈፀሙም ይታወቃል።
ወንበራ ወረዳ ላይ መከላከያውን ጨምሮ መንግስታዊ ያልሆኑ የድርጅህ ሰራተኞች ላይ ሳይቀር ጥቃት ፈፅሟል::

በጥር 1 እና 2/2013/ዓ.ም በአማራ ክልል ውስጥ እየገባም ሰብል አቃጥሏል::በአማራና በቤኒሻንጉል ድንበሮች ላይ ማለትም በመንታውሀ በነጭ ድንጋይ ፣ በየጨረቃ አካባቢ እየገቡ የአማራውን የሰብል ክምሮች እያቃጠሉ ይገኛሉ::ሰብላቸው የተቃጠለባቸው ሰዋች የሚያቃጥሉትን ተከታትለው እርምጃ ለመውሰድ ቢሞክሩም መከላከያ ከጉምዞች ጋር መወገኑን ሰምተናል።

በነዚህ አካባቢዋች ሰብላቸው ከተቃጠለባቸው ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው:-
1.መዲና ሀሰን 3 ሄክታር በቆሎ.
2 . ከድር: 2 ሄክታር ሆቾሎኒ
3.ኢሳ በላይ: 1 ሄክታር በቆሎ
4.ሸህ ሁሴን እንድሪስ: 3 ሄክታር ጤፍ
5.አደም በዜ: / 3 ሄክታር በቆሎ/
6.ሲራጅ የሱፍ: 2 ሄክታር ኦቾሎኒ
7.አደም ሲራጅ: 1 ሄክታር ዳጉሳ
8.ጎበዜ አሊ: 2 ሄክታር ዳጉሳ
9.ሞሚናት ሀሰን: 1ሄክታር ኦቾሎኒ
10.አራገው ተገኘ :2ሄክታር ዳጉሳ
11.ሙሀመድ ሰይድ: 2ሄክታር በቆሎ
12.እስሌማን ሀሰን: 3ሄክታር በቆሎ
13.ይብሬ ጫኔ:በቆሎ ኦቾሎኒ ዳጉሳ/ 3 ሄክታር
14 እስሌማን ይብሬ: 1ሄክታር ዳጉሳ
15.ታደሰ መንገሻ: 60 ኩንታል: 2ሄክታር በቆሎ
16.አቡ አሊ: 60 ኩንታል/ 2 ሄክታር ጤፍ
17.ኢብራሂም ሰይድ:2ሄክታር በቆሎ
18.አብደላ መሀመድ:3 ሄክታር በቆሎ
19.እንድሪስ መሀመድ:1ሄክታር ዳጉሳ
20.ሸህ አብደላ አሊ: ግማሽ ሄክታር በቆሎ
21.እንድሪስ አብደላ:ግማሽ ሄክታር በቆሎ
22.ደብር ጌታቸው: ግማሽ ሄክታር በቆሎ
23.ክንዱ ሰይድ:2ሄክታር በቆሎ
24.እስማኤል ቀዮ:2ሄክተር ጤፍ
25.አደም አህመድ: ሁለት ሄክታር ኦቾሎኒ ሙሉ በሙሉ ወድሟል።

በሌላ በኩል የቤኒሻንጉልን ሰላም አሰፍናለሁ ያለው የአባገዳ አባገዳ እና መንግስት ሰላም አሰፍናለሁ ብሎ መተከል ከከተመ ሰነበተ ግድያው ግን ተባብሶ ቀጥሏል::