ሀገራዊ ስካሩ በቀላሉ የሚበርድ አይደለም፤ ሁሉም በውጣልኝ ጥንብዝ ብሎ ሰክሯል – ዶክተር ወዳጄነህ መሃረነ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ

የሕክምና ዶክተር እና የሥነ ልቦና አማካሪ፣ አነቃቂ ንግግሮችን በማድረግም የሚታወቁት ዶክተር ወዳጄነህ መሃረነ ይናገራሉ

👉 በተሰራብን ያልተገባ አስተሳሰብ ምክንያት ሀገር ለማረጋጋት ቀርቶ ራስን ለማኖር እንኳን አያስችልም

👉 ሀገራዊ ስካሩ በቀላሉ የሚበርድ አይደለም፤ ሁሉም በውጣልኝ ጥንብዝ ብሎ ሰክሯል፤

👉 አንዳንዶች ላይ ስካሩ ከመጠን አልፎ በጅምላ ጨፍጭፎ መቅበርን ተግባራዊ አደረጉት፣

👉 የስካሩ መጠን ሰው ማረድን ከእንስሳት እስከአለመለየት አድርሷል፤

👉 የፖለቲካ ሰዎቻችን ቢረጋጉ፣ በውይይት ችግሮቻቸውን ለመፍታት ቢሞክሩ፤ ወደ ማስተዋል ቢመጡ፤ በየፌስቡኩ ላይ ባይሰዳደቡ፣ እልህ ውስጥ ባይገቡ፣ ለትውልዱ ቢያስቡ መልካም ነገሮች ይመጣሉ፤

👉 ይቅርታን ማስቀደም፣ የተቸገሩትን መርዳት፣ መራራቅን ማስወገድ፣ መቀራረብን ማጠንከር ያሰፈልጋል፤

👉 ለሁሉም ነገር ማሰሪያችንም መጀመሪያችንም ፍቅር ይሁን፤

👉 መከባበር፣ ሜዳ ላይ የወደቁትን ማንሳትና መደገፍ፣ ጥላችንን ማስወገድ ይኖርብናል፤

👉 የፖለቲካ ጣልቃ ገብነትና ጫና በሃይማኖቶች ላይ መኖርም የፖለቲካ ሰዎች ሃይማኖትን ለራሳቸው ጥቅም ለማዋላቸው ምክንያት እየሆነ ነው፤

👉 የሃይማኖት መሪዎችና የፖለቲካ ሰዎች አላስፈላጊ ቅርርብ አድርገው የፖለቲካው ተጽዕኖ ወደ ሃይማኖቱ እንዲጋባ መደረጉም ሌላው ችግር ነው፣

👉 ከሁሉም በላይ የፖለቲካ ሰዎች ሕዝቡን በሚያገኙበት ሁሉ የእነርሱ ሀሳብ ትልቅ ቦታ እንዲያገኝ መሻታቸውና መስራታቸው ጥላቻና ውጣልኝን አበራክቷል፤

👉 ኢትዮጵያዊ መልካችንንም የቀየረው ይኸው አስተሳሰባችን ነው፣

👉 ትውልድ መቅረጽ ቀላል ነው፤ ይህንን የሚተገብር አመራር ከፌዴራል እስከ ቀበሌ ድረስ ካለ የዛሬ ችግሮች ቦታ አያገኙም፤

👉 አሁን ያለው ችግር ሁሉም ነገር ችግር ያለበት ነው፤ በአንድ ሀሳብ መስማማት ቀርቷል፤

👉 የሕገመንግሥቱ መቀየር፣ መሻሻል፣ የፖለቲካ መሪዎች መቀያየር ወዘተ ለመፍትሄ የሚያቀራርብ አይደለም፤

👉 ሁሉም ተቃራኒ ጉዳይ ስላለበት በዚያም በዚህም ተከልሏል፤

ከዶክተር ወዳጄነህ መሃረነ ጋር የተደረገውን ሙሉ ቃለ ምልልስ ከታች ካለው ሊንክ ያገኙታል
https://www.press.et/Ama/?p=39040