በራያ አላማጣ ደሞዝ የሚጠብቁ የመንግሥት ሠራተኞች 

በራያ አላማጣ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች ካለፉት 3 ወራት ጀምሮ ደመወዝ አላገኘንም ሲሉ አማረሩ። ከአላማጣ አስተያየታቸውን ለዶቼቬለ የሰጡት የመንግሥት ሠራተኞቹ እንዳሉት መንግሥት በትግራይ ሲያካሂድ የነበረውን የሕግ ማስጠበቅ ዘመቻን ተከትሎ ባለፉት ወራቶች ደመወዝ ባለመቀበላችን ለከፋ ችግር ተጋልጠናል ብለዋል። …