በተደጋጋሚ 72 ሰአት የሚሉት ስለተሸነፉ ነው እኛ ፈጽሞ ጊዜ ልንሰጣቸው አይገባም – የዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የትግርኛ መግለጫ


የመረጃ ቲቪን 24/7 የሳተላይት ስርጭት በመደገፍ የኢትዮጵያ ህዝብ አማራጭ እና ትክክለኛ መረጃ በማግኘት እራሱን ከተጋረጠበት አደጋ መከላከል እንዲችል እናግዝ። በአሁኑ ወቅት ከመረጃ ቲቪ በስተቀር ሌሎች ሁሉም በኢትዮጵያ ያሉ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የመንግስት የፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ናቸው። ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ የከፈትነው የመረጃ ቲቪ የሳተላይት ስርጭት የአንድ ዓመት ወጪን ለመሸፈን ነው። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን ድጋፍዎትን ይለግሱ » https://gofund.me/54405070
የዛሬው የዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የትግርኛ መግለጫ ሲጠቃለል
1. በዚህ ጦርነት መቶ በመቶ ከአማራ ልዩ ሃይል ጋር ነው የገጠምነው፣ መቶ ፐርሰት ከኤርትራ ጦር ጋር ነው የገጠምነው፣መቶ በመቶ ከአብይ ጦር ጋር ነው የገጠምነው።
2. ምጥጥኑን ስንመለከት አንድ የትግራይ ወታደር ለሁለት ክፍለጦር የሚግጥም ሲሆን ገጥሞም እያሸነፈው ነው።
3. አሁን በተደጋጋሚ 72 ሰአት የሚሉት ስለተሸነፉ ነው። እኛ ፈጽሞ ጊዜ ልንሰጣቸው አይገባም።
4. ውጭ የምትኖሩ ኤርትራዊያን በተቃውሞ አግዙን ።
5. ውሸት እየሰማችሁ አትረበሹ። እያሸነፍናቸው ነው። በተለይ የአድዋና አክሱም መያዝ ብዙ ሰውን አስደንግጧል፣ አትደንግጡ።