በደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት የተላኩ ልዑካን መንግስትና ወንጀለኛው ሕወሓትን ለማደራደር ይመጣሉ የተባለው ሐሰት ነው – መንግስት


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ከደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንትና ከወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር ራማፎሳ የተላኩ ልዑካንን ተቀብለው በቀጣናው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት እንደሚያደርጉ ከመንግስት ተሰምቷል።የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ መረጃ ማጣርያ ጠ/ሚር አብይ አህመድ በደቡብ አፍሪካው ፕሬዝደንት ሳይሪል ራማፎዞ የተመረጡትን ሶስት ልዩ መልእክተኞች ተቀብለው አንድ በአንድ እንደሚያነጋግሩ ገልጿል።

የ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ዛሬ ጠዋት በለቀቀው መረጃ መሰረት ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት የተላኩ ልዑካን የፌዴራሉን መንግስትና ወንጀለኛው ሕወሓትን ለማደራደር ነው የሚሉ ዘገባዎች ሐሰት ናቸው ብሏል።“ልዩ መልእክተኞቹ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው በመንግስትና በወንጀለኞቹ መሀል ሽምግልና ያካሂዳሉ የተባለው ሀሰት ነው” ብሏል።በደቡብ አፍሪካው ፕሬዝደንት የተመረጡት ሶስቱ መልእክተኞች የቀድሞዋ የላይቤርያ ፕሬዝደንት ኤለን ጆንሰን-ሰርሊፍ፣ የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝደንት ጋሌማ ሞትላንቴ እና የቀድሞው የሞዛምቢክ ፕሬዝደንት ጆአኪም ቺሳኖ ናቸው።