የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር እና የትግራይ የፖለቲካ ፓርቲዎች መማከራቸው ተሰማ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክር ቤት በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ ሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር አካሂዷል።
በምክክር መድረኩ ላይ በጊዜያዊ አስተዳደሩ መሪነት በክልሉ ሰላም ለማምጣት በሚደረጉ ጥረቶች ውስጥ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳትፎ ምን መሆን አለበት የሚል ሐሳብ ተነሥቷል።
በክልሉ ሊሠሩ የታሰቡ ዐበይት ሥራዎች የተገለጹ ሲሆን፣ ባለ ስድስት ነጥብ ረቂቅ ቻርተር ዝግጅት መደረጉ ታውቋል።
እነዚህም የአስተዳደር መዋቅር ማስተካከል፣ የክልሉ ሰላም እና ደኅንነት ማስጠበቅ እና ማረጋገጥ፣ ፍትሕ እና መልካም አስተዳደር ማስጠበቅ እና ማረጋገጥ፣ የተቋረጠውን ማኅበራዊ አገልግሎት ማስቀጠል፣ የክልሉን ኢኮኖሚ እንዲያገገም ማድረግ እንዲሁም በቀጣይ ከሚካሄደው 6ኛው አገራዊ ምርጫ ጋር በተያያዘ በክልሉ ውስጥ መንቀሳቀስ ለሚፈልጉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሐሳባቸውን በነፃነት አቅርበው እንዲወዳደሩ የፖለቲካ ምኅዳሩን ማመቻቸት ሥራዎች መሆናቸው ተዘርዝሯል።
ፓርቲዎቹ በአሁኑ ወቅት በክልሉ እየተካሄደ ላለው ሕግ የማስከበር ዘመቻ ግብ እስኪመታ ከመንግሥት እና ከመከላከያ ኃይል ጎን እንዲቆሙ ተጠይቋል። EBC