ፀጥታን የማደፍረስ ውጥኖች መክሸፋቸውን የኦሮሚያ ክልል ዐስታወቀ፡፡


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


DW : በኦሮሚያ ክልል ባለፉት ሁለት ሳምንታት ማለትም በትግራይ ክልል «የሕግ የበላይነትን ለማስከበር» ርምጃ እንዲወሰድ ታውጆ ወደ ውጊያ ከተገባ ወዲህ የተለያዩ ፀጥታን የማደፍረስ ውጥኖች መክሸፋቸውን ክልሉ ዐስታወቀ፡፡

የክልሉ የአስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ጅብሪል መሓመድ ለዶይቼ ቬሌ (DW) እንዳሉት በዚህን ወቅት በኦሮሚያ «የኦነግ ሸኔ» ያሏቸው ሸማቂዎች በሚንቀሳቀሱበት አከባቢ ቢያንስ 200 ታጣቂዎች ላይ እስር እና የኃይል እርምጃ መወሰዱን ጠቅሰዋል። ታጣቂዎቹ ላይ ርምጃ የተወሰደው፦ «ጉሊሶ ላይ አደጋ ካደረሱ በኋላ» በአጸፌታ መኾኑን ኃላፊው አክለው ተናግረዋል።

ከሁለት ሳምንታት በፊት በምስራቅና ምዕራብ ወለጋ የመከላከያ ሰራዊት ለቀው በመውጣቱ ነዋሪዎች ስጋት ላይ ወድቀው መቆየታቸውን ያልሸሸጉት ኃላፊው በአከባቢው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ኃላፊነቱን ተቀብሎ፤ በአሁኑ ወቅት የተረጋጋ ሁኔታ መኖሩን አውስተዋል፡፡ ኃላፊው አክለውም የኦሮሚያ ክልል ባለው 7 ሺህ ገደማ ቀበሌዎች ሁሉ ትምህርት ለማስጀመር ስጋት የሚሆን የፀጥታ ችግር አለመኖሩን ነው ያረጋገጡት፡፡