በርካታ ሰራዊት የያዘው የሱዳን ሰራዊት በኮርሁመር በኩል አዲስ ወረራ ጀምሯል።

ሕዝብ በሁለት አቅጣጫ እየተወጋ ነው!

መቀሌ ቢሮ የተከፈተላቸው የቅማንት ኮሚቴ ነን የሚሉት ትዕዛዝ ዛሬ መንገድ ተዘግቶ ውሏል። ወደ መተማ ሲያልፉ የነበሩ አስራ አራት መኪናዎች ተሰባብረዋል። የዜጎች ቤት እየተመታ ነው። መከላከያ ሰራዊትና የአማራ ልዩ ሀይል አካባቢውን ማረጋጋት አልቻለም።

በሌላ በኩል ደግሞ ዛሬ የሱዳን ሰራዊት እንደ አዲስ ወረራ ጀምሯል። በርካታ ሰራዊት የያዘው የሱዳን ሰራዊት በኮርሁመር በኩል መግባቱ ተገልፆአል።

ሕዝብ ከፊትና ከጀርባ እየተወጋ ነው። ወደመተማ የሚወስደው መንገድ ባለፉት ሳምንታትም ተጓዦችን ለአደጋ ያጋለጠ የነበር ሲሆን ዛሬ የባሰ ሆኗል። የመተማ ወረዳ ነዋሪዎችም “መንግስት ችግሩን ማብረድ ካልቻለ አማራጭ እንወስዳለን” በማለታቸው እስከ ነገ አራት ሰዓት ታገሱ መባላቸው ታውቋል።

የሱዳን ወረራ

ዛሬ ሀምሌ 25/ 2010 ዓም ከቀኑ 7 ሰዓት በሆሩመር ምድርያ በኩል የሱዳን ሰራዊት የአማራ ገበሬዎችን ወርሯል። ማሳቸው ላይ የነበሩት ገበሬዎች ላይ ወረራ የፈፀመው የሱዳን ሰራዊት ከወንድሙ ማሳ የነበረውን አንድ ተማሪ አቁስሏል።

የአማራ ገበሬዎች ከባድ መሳርያ የታጠቀውና በርካታ ሰራዊት ያለው የሱዳን ጦርን የተከላከሉ ሲሆን አንድ ትራክተር፣ አንድ 3 ኤፍ መኪና እና አንድ ዲሽቃን ጨምሮ መማረካቸው ታውቋል። የሱዳን ሰራዊት ኃይል አጠናክሮ ሲመጣ ከተማረኩት መካከል 3 ኤፍ መኪና እና ዲሽቃውን ገበሬዎቹ አውድመዋል። ትራክተሩ ወደ ሆሩመር ከተማ ተወስዷል።

የተወሰነ ቁጥር ያለው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በአካባቢው ቢኖርም የአማራ ገበሬዎችን አላገዘም።መረጃ ቲቪን በተሻለ ጥራት እና ፍጥነት እንድናቀርብ እገዛችሁን እንሻለን።
መረጃ ቲቪን ለማገዝ ይህን ሊንክ በመጫን አባል ይህኑ - JOIN Mereja TV