በአገሪቷ የተፈጠረው ሁኔታ ከጦርነት ይልቅ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ወንጀለኞችን ለፍርድ የማቅረብ ኦፕሬሽን ነው – የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የኮሚኒኬሽን ቡድን ቃል አቀባይ

Capital – አዲስ የተቋቋመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የኮሚኒኬሽን ቡድን ቃል አቀባይ የሆኑት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን አሁን በአገሪቷ የተፈጠረው ሁኔታ ከጦርነት ይልቅ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ወንጀለኞችን ለፍርድ የማቅረብ ኦፕሬሽን ነው አሉ
ጎረቤት አገራትም የኢትዮጵያ መንግሥት ሁኔታን በመረዳት ለመንግስት ድጋፍ እንደሚያደርጉ የገለጹት አምባሳደር ሬድዋን ጅቡቲ፣ ሱዳን እና ኤርትራ ከመንግሥት ጎን ቆመዋል፡፡
በዚህም ኤርትራ ራሷን ወደ ጦርነት በማስገባት ተሳታፊ እንደማትሆን ገልጸው፤ ነገር ግን ድንበር አልፈው ለሚመጡ ንፁሃን ዜጎችን እንደምትቀበል ተናግረዋል፡፡
አዲስ የተቋቋመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የኮሚኒኬሽን ቡድን ቃል አቀባይ የሆኑት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እንደገለጹት አሁን በሀገሪቷ የተፈጠረው ሁኔታ ከጦርነት ይልቅ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ወንጀለኞችን ለፍርድ የማቅረብ ኦፕሬሽን ነው ብለዋል፡፡
ጎረቤት አገራትም የኢትዮጲያ መንግሥት ሁኔታን በመረዳት ለመንግስት ድጋፍ እንደሚያደርጉ የገለጹት አምባሳደር ሬድዋን ጅቡቲ፣ ሱዳን እና ኤርትራ ከመንግሥት ጎን ቆመዋል፡፡
በዚህም ኤርትራ ራሷን ወደ ጦርነት በማስገባት ተሳታፊ እንደማትሆን ገልጸው ነገር ግን ድንበር አልፈው ለሚመጡ ንጹሐን ዜጎችን እንደምትቀበል አስታውቀዋል፡፡
በጅቡቲ በኩልም ማንኛወም የጦር ወንጀለኛ ወደ ጅቡቲ የሚያሸሹ ካለ ለኢትዮጵያ መንግሥት ለማስረከብ ቃል በመግባት እየሰሩ ሲሆን በተጨማሪም ገቢ እና ወጪ እቃዎች ላይ ጉዳት እንዳደርስ ተገቢውን ጥበቃ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡
ሱዳን በበኩሏ በትግራይ በኩል የሚያዋስናትን ድንበር ሕገወጥ መሣሪዎችን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር ሲባል ድንበሯን ዘግታለች፡፡
በተጫማሪም አምባሳደር ሬድዋን መንግሥት ባለፉት ጊዜያት ወደ ውይይት በመምጣት ነገሮችን ለማረጋጋት ሙከራዎችን ቢያደርግም ውጤት አላመጣም ሲሉ ከአሁን በኋላ ግን በውይይት ለመፍታት እንደማይሠራ፤ ይልቁንስ አሁን የተፈጠረው ሁኔታ አገርን መካድ መከላከያ ሰራዊት ላይ ያልታሰበ ጥቃት በማድረስ ጉዳት ማስከተልና መሳሪያዎችንም መንጠቅ ሲሆን ቡድኑን ወደ ሕግ በማምጣት ሕገ መንግሥቱን ማስከበር እስካልተቻለ ድረስ በእጁ የገቡትን መሣሪያዎች ማጥፋት እስካልተቻለ ድረስ ለአገር ህልውና አስጊ ነው ብለዋል፡፡
በጅቡቲ በኩልም ማንኛውም የጦር ወንጀለኛ ወደ ጅቡቲ የሚያሸሹ ካለ ለኢትዮጲያ መንግስት ለማስረከብ ቃል በመግባት እየሰሩ ሲሆን በተጨማሪም ገቢ እና ወጪ እቃዎች ላይ ጉዳት እንዳደርስ ተገቢውን ጥበቃ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡
ሱዳን በበኩሏ በትግራይ በኩል የሚያዋስናትን ድንበር ሕገወጥ መሣሪዎችን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር ሲባል ድንበሯን ዘግታለች፡፡
በተጨማሪም አምባሳደር ሬድዋን መንግሥት ባለፉት ጊዜያት ወደ ውይይት በመምጣት ነገሮችን ለማረጋጋት ሙከራዎችን ቢያደርግም ውጤት አላመጣም ሲሉ ከአሁን በኋላ ግን በውይይት ለመፍታት አንደማይሰራ ይግልፃሉ ይልቁንስ አሁን የተፈጠረው ሁኔታ አገርን መካድ መከላከያ ሠራዊት ላይ ያልታሰበ ጥቃት በማድረስ ጉዳት ማስከተልና መሳሪያዎችንም መንጠቅ ሲሆን ቡድኑን ወደ ሕግ በማምጣት ሕገ መንግሥቱን ማስከበር እስካልተቻለ ድረስ በእጁ የገቡትን መሣሪያዎች ማጥፋት እስካልተቻለ ድረስ ለአገር ህልውና አስጊ ነው ይላሉ፡፡