የመንግሥት የሥራ ሓላፊዎች አስፈላጊው የሕግ ማጣራት እንዲደረግባቸው የስም ዝርዝርቸውን ለፌዴራል ፖሊስ ሊተላለፍ ነው


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የፌዴራል ሥነምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ሀብት እና ንብረታቸውን ያላስመዘገቡ 100 የፌዴራል እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት የሥራ ሓላፊዎች አስፈላጊው የሕግ ማጣራት እንዲደረግባቸው የስም ዝርዝርቸውን ለፌዴራል ፖሊስ እንደሚያስተላልፍ አስታወቀ።
የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ወዶ አጦ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሓላፊዎች አንድ ሺህ ብር እየተቀጡ ሀብት እና ንብረታቸውን እንዲያስመዘግቡ የተቀመጠው የጊዜ ገደብ እስከ ዛሬ 11 ሰዓት ከ30 ድረስ ብቻ መሆኑን ለኢዜአ ተናግረዋል።
በተሰጠው የጊዜ ገደብ ሀብት ንብረታቸውን ካላስመዘገቡ 180 የፌዴራል መንግስት እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ ሓላፊዎች መካከል 80ዎቹ አንድ ሺህ ብር ቅጣት ተጥሎባቸው ሀብት ንብረታቸውን ማስመዝገባቸውንም ጠቅሰዋል።
ቀሪዎቹ 100 የመንግሥት የሥራ ሓላፊዎች ግን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ሀብት ንብረታቸውን ባለማስዘግባቸው አስፈላጊው የሕግ ማጣራት እንዲደረግባቸው ለፌዴራል ፖሊስ የስም ዝርዝራቸው እንደሚተላለፍ ምክትል ኮሚሽነሩ ገልጸው፣ በቀሩት ሰዓታት ውስጥ ሀብት እና ንብረታቸውን እንዲያስመዘግቡ ጥሪ አቅርበዋል።