በሳውዲ አረቢያ እስር ቤቶች የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ጉዳይ በቅርቡ እንደሚፈታ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታወቀ።

በሳውዲ አረቢያ እስር ቤቶች የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ጉዳይ በቅርቡ እንደሚፈታ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታወቀ።
Image may contain: 1 person, sittingየሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ላለፉት 20 ቀናት በሰራቸው ጉዳዮች ላይ ማብራሪያን ሰተዋል።
ኢትዮጲያ በ75 ተኛው የተባበሩት መንግስት ድርጅት የነበራትን ተሳትፎ ፣የሚኒስቴሩ የልኡካን ቡድን በሱዳን ስላደረገው መጠነኛ እርዳታና ገብኝት እንዲሁም በቅርቡ ስለተከናወኑ የአምባሳደር ሹመቶች ላይ ገለፃ ተደርጓል።
በተጨማሪም በዚህ ሳምንት ውስጥ ከ 900 በላይ ዜጎች ከውጪ ሃገራት ስለ መመለሳቸው ተነግሯል።
በጋዜጠኞችም በተደጋጋሚ በሳውዲ በእስር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ያሉበት ሁኔታ ምን ይመስላል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ታሳሪዎቹ ካሉበት ሁኔታ ነፃ ለማውጣትስ ምን እየሰራ ነው ?የሚለው ጉዳይ በተደጋጋሚ ተነስቷል።
በሳውዲ ብቻም ሳይሆን በተለያዩ መካከለኛው ምስራቅ ሃገራት የሚገኙ ዜጎች ጉዳይ አሳዛኝና መፍትሄ ሊበጅለት የሚገባ ነው ያሉት አምባሳደር ዲና ከሃገራቱ ጋር የሚደረጉ ውይይቶችን በማድረግ ችግሩን ለመፍታት እንደሚሰራ ተናግረዋል።
ሌላው በመግለጫው ላይ የተነሳው የኢትዮ ኤርትራ ግንኙነት ጉዳይ ሲሆን የፕረዝደንት ኢሳያስ አፍወርቂ ጉብኝት አላማና ሃገራቱ ያልተቋጩ የዲፕሎማሲ ጉዳዬች በተለይም በድንበር ጉዳይ ላይ ምን ታስቧል? ተብሎ ለተነሳው ጥያቄ ሃገራቱ በጊዜ ሂደት ያላቸው ግንኙነት እየ ዳበረ መምጣቱና በቀጣይም የተሻለ ቅርርቦሽ እንዲኖር እየተሰራ መሆኑን አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናግረዋል።