በኮቪድ ተይዘዋል የተባሉ የተመረመሩ የኢትዮጵያ አምባሳደሮች ቁጥር አልታወቀም ተባለ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ቁጥሩን ባላውቀውም 21 ግን እንዳልሆኑ እርግጠኛ ነኝ – አምባሳደሮች ስልጠና ላይ ተሳታፊ ከነበሩ

21 አምባሳደሮች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል ?

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ “በቢሾፍቱ ከተማ ስልጠና ላይ ከነበሩ አምባሳደሮች መካከል ሃያ አንዱ (21) በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ታውቋል ፣ እንዲሁም የUN አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ወደ ኒው ዮርክ አይመለሱም” የሚል መረጃ በስፋት እየተሰራጨ ተመልክተናል።

በዚህ ጉዳዩ ላይ ስማቸውን የማንገልፅላችሁ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመራሮች/እንዲሁም በስልጠናው ላይ ተሳታፊ ከነበሩት መካከል አንድ ሰው ተከታዩን ብለውናል ፦

“አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ወደ New York ትላንትና እንደሚበሩ ነግረውኛል። አዲስ ነገር አልሰማሁም። 21 አምባሳደሮች በCOVID-19 አልተያዙም።

ነገር ግን ከስብሰባችን በኋላ አንዴ ከመውጣታችን በፊት ከዛም አርብ እለት ምርመራ አድርገናል ነገር ግን የጤና መረጃ የግል confidential ስለሆነ በትክክል ቁጥሩን መናገር አልችልም።

ከአምባሳደሮቻችን መካከል ወደ አስራ አምስት (15) የሚሆኑ ወደየሚሰሩበት ሀገር ተመልሰዋል። አሁን ደግሞ እዚህ MINT ያዘጋጀው program ላይ አብዛኞቻችን አለን።

ቁጥሩን ባላውቀውም 21 ግን እንዳልሆኑ እርግጠኛ ነኝ ከላይ በጠቀስኩት ምክንያት።

Source – tikvah ethiopia

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ “በቢሾፍቱ ከተማ ስልጠና ላይ ከነበሩ አምባሳደሮች መካከል ሃያ አንዱ (21) በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው  የሚል የተሰራጨ መረጃ