ኢትዮጵያ አዲሱን የ200 ብር ኖትና አዲስ የገንዘብ ዓይነቶች ይፋ አደረገች


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ኢትዮጵያ ነባሮቹን የ10፣ የ50 እና የ100 የብር ኖቶች የሚተኩ አዲስ የገንዘብ ዓይነቶችና አዲሱን የ200 ብር ኖት ይፋ አደረገች
(ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ ነባሮቹን የ10፣ የ50 እና የ100 ብር ኖቶች ዓይነቶችን ሙሉ ለሙሉ በመተካት ለግብይት የሚሆን አዲስ የብር ኖት መጠቀም እንደምትጀምር ይፋ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ።
ነባሮቹን የብር ኖቶች ከሚተኩት በተጨማሪ በዛሬው ዕለት የ200 ብር ኖት ይፋ እንደሆነ ነው ጠቅላይ ሚኒስትትር ዶክተር ዐቢይ በፌስቡክ ገፃቸው ባወጡት መረጃ የገለፁት።

እነዚህ አዲስ የገንዘብ ዓይነቶች ለሕገ ወጥ እንቅስቃሴዎች የሚደረግን ድጋፍ፣ ሙስናን እና የኮንትሮባንድ ሥራዎችን ለመቀልበስ እንደሚረዱ ተጠቁሟል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲሶቹ የገንዘብ ዓይነቶች ላይ የተካተቱ መለያዎች አመሳስሎ ገንዘብ ለማተም የሚደረጉ ሕገ ወጥ ጥረቶችንም ለማስቀረት እንደሚያግዙ ገልፀዋል።
አዲስ የታተሙት የብር ኖቶቹ በአካላቸው ላይ የሚገኙ የደህንነት መጠበቂያ ምልክቶች ያሉባቸው ናቸው።
እነዚህን ያላሟሉ ወይም ተመሳስለው የተዘጋጁ ገንዘቦች የያዙ ወይም የሚጠቀሙ ግለሰቦች ካጋጠሙ ለፀጥታ አካላት መጠቆም እንደሚገባ ተነግሯል
አሁኑ ወቅት በሥራ ላይ የሚገኙት የብር ኖቶች ወደ ዝውውር እንዲገቡ የተደረጉት ከ23 ዓመት በፊት በ1990 ዓ.ም ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነትን ተከትሎ እንደነበረ ይታወሳል።
ከአጼ ኃይለ ሥላሴ አስተዳደር ዘመን ጀምሮ በኢትዮጵያ ሥራ ላይ በነበሩ የገንዘብ የወረቀት ገንዘቦች ላይ በተለያዩ ጊዜያት ለውጥ የተደረገ ሲሆን፤ ወደ አምሳ ዓመታት በሚጠጋው የንጉሡ የሥልጣን ዘመን አራት ጊዜ የብር ኖቶች ለውጥ ተደርጓል።
ወታደራዊው መንግሥት ዘውዳዊውን ሥርዓት አስወግዶ አገሪቱን መምራት ከጀመረ ከጥቂት ዓመታት በኋላ በ1969 ዓ.ም የንጉሡ ምስልን የያዙትን የመገበያያ ገንዘቦች ለውጦት ቆይቷል።
በተመሳሳይም ኢህአዴግ ደርግን አስወግዶ አገሪቱን ከተቆጣጠረ በኋላም ለሰባት ዓመታት ያህል ቀድሞ የነበረውን ገንዘብ ሲጠቀም ቆይቶ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የድንበር ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ በአጭር ጊዜ ውስጥ የብር ኖቶቹ እንዲቀየሩ አድርጓል።