ተስፋና ስጋት – የዘንድሮው ዓመት ከአምናው ያደሩ መፍትሄ ያልታየባቸው ችግሮችን ወርሷል።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


«የ2012 ቅኝት፤ የ2013 ተስፋና ስጋት» – ከ2012 ወደ 2013ዓ,ም

DW : 2012 ዓ,ም ሥራውን ሠርቶ ተራውን ለ2013 አስረክቧል። 2012 ዓ,ም በኢትዮጵያ አሳሳቢ፣ አሳዛኝ አሰቃቂያና አስጊ ክስተቶች ተፈራርቀዋል።

በተቃራኒው አዎንታዊ እና ለትውልድ የሚሻገሩ የጥረት ውጤት የሆኑ የልማት ሥራዎችም ተከናውነዋል።

አዲስ ዓመት አዲስ ተስፋን የሚጭር የመሆኑን ያህል የዘንድሮው ዓመት ከአምናው ያደሩ መፍትሄ ያልታየባቸው ችግሮችን ወርሷል። ይህን በማሰብ በእርግጥ ወደ አዲስ ዓመት ተሸጋገርን ማለት ይቻል ይሆን? የሚሉ ጥቂት አይደሉም።

ጊዜ ለሁሉ ምላሽ አለውና በአዲሱ ዓመት የመጀመሪያ የእንወያይ እንግዶችን ጋብዘን 2012ን ወደኋላ በመፈተሽ የ2013 ዓ,ምን ተስፋና ስጋት ቃኝተናል።