አዲስ አበባ ወደ ራስ ገዝ አስተዳደርነት እንድታድግ ባልደራስ ትግሉን ከፍ ወዳለ ምእራፍ አሳደገ


የመረጃ ቲቪን 24/7 የሳተላይት ስርጭት በመደገፍ የኢትዮጵያ ህዝብ አማራጭ እና ትክክለኛ መረጃ በማግኘት እራሱን ከተጋረጠበት አደጋ መከላከል እንዲችል እናግዝ። በአሁኑ ወቅት ከመረጃ ቲቪ በስተቀር ሌሎች ሁሉም በኢትዮጵያ ያሉ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የመንግስት የፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ናቸው። ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ የከፈትነው የመረጃ ቲቪ የሳተላይት ስርጭት የአንድ ዓመት ወጪን ለመሸፈን ነው። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን ድጋፍዎትን ይለግሱ » https://gofund.me/54405070
ዜና ባልደራስ!
አዲስ አበባ ወደ ራስ ገዝ አስተዳደርነት እንድታድግ ባልደራስ ትግሉን ከፍ ወዳለ ምእራፍ አሳደገ!
አዲስ አበባ ራስ ገዝ ( ክልል በአሁኑ አጠራር) እንድትሆን ባልደራስ በፕሮግራሙ ላይ አስቀምጦ እየታገለ መሆኑ ይታወቃል:: ይህንን ዓላማውን ተግባራዊ ለማድረግ ስራ አስፈፃሚው አንድ ግብረ ሃይል በማቋቋም እንቅስቃሴዎች እንዲጀመሩ ወስኗል።
ዝርዝር ጉዳዮችን በተመለከተ የፊታችን ማክሰኞ ጳጉሜ 3 ቀን 2012 ዓ/ም ከጠዋቱ በ4 ሰዓት ጋዜጣዊ መግለጫ በዋና ፅ/ቤቱ የሚሰጥ ሲሆን በመግለጫው ላይ÷
የሰላማዊ ትግሉ አቅጣጫዎች በዝርዝር. ይተነተናሉ
ለዚህ አላማ የትብብር ጥሪም ይቀርባል
ድል ለዴሞክራሲ!