ማእከላዊ የደረሰባቸውን ሰቆቃ የተናገሩ እስረኞች በችሎት መድፈር ስም 6 ወር እየተፈረደባቸው ነው ።

አስቻለውን ፍቱት!

አስቻለው ደሴ ባህርዳር ተያዘ። ማዕከላዊ ወስደው አኮላሹት። በአርበኞች ግንቦት 7 ክስ አቀረቡበት። ፍርድ ቤት እንኳ በደሉን እንዲናገር አልተፈቀደለትም! በቃል መናገር ሲከለከልም ሱሪውን አውልቆ የተኮላሸውን አሳይቷል።

በደሉን በቃሉ እንዳይናገር የተከለከለው አስቻለው ሱሪውን አውልቆ የተኮላሸውን ብልቱን በማሳየቱ ቂሊንጦ እስር ቤት ቀጥቶታል። ጨለማ ቤት አስገብቶታል። ሕክምና ተከልክሏል።

ማዕከላዊ ተዘጋ ተብሎ በዛ ስቃይ ቤት መከራ የደረሰበት አስቻለው ደሴ አልተፈታም። እስረኛ ይፈታል ተብሎ ሰቆቃ የደረሰበት አስቻለው አሁንም በቂሊንጦ ሰቆቃን እየተቀበለ ነው። አርበኞች ግንቦት 7 ስሙ ከፀረ ሽብር አዋጁ ተነሳ ተብሎ በድርጅቱ ስም የተከሰሰው አስቻለው በእስር ላይ ነው።

በቅርቡ ደግሞ አስቻለው እንዳይፈታ የፈለጉት አካላት ፍርድ ቤት ወስደው “ችሎት ደፍረሃል” ብለው 6 ወር አስፈርደውበታል። ችሎት መድፈር የሚሉት እስረኛ ማዕከላዊና ቂሊንጦ የደረሰበትን በደል፣ የፍርድ ቤቱን ችግር በግልፅ ሲናገር ነው!

ይህ ሁሉ ስቃይ የደረሰበትን አስቻለው ደሴን ፍቱት!