ብአዴን ብአዴን ነው! አይድንም! (ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው)

ብአዴን ብአዴን ነው! አይድንም! (ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው)

“ አማራ ልማቱም ውድቀቱም በራሱ ልጆች እጅ ነው ያለው፣ ኦሮሞ ልማቱም ውድቀቱም በራሱ ልጆች እጅ ነው ያለው፡፡……”አቶ በረከት ስምኦን በ2008 ዓም ለከፍተኛ አመራሮች የሰጠው ስልጠና ላይ

‹‹በአማራ ክልል ሰላም እንዲናጋ ህወሀት ምክንያት ሊሆን አይችልም፡፡የደገፍነው ለውጥ እንዲጠፋ የሚፈልግ የውጭ ሀይል የለም፡፡ ጥፋቱም ልማቱም የሚወሰነው በእኛው ነው››

ገዱ አንዳርጋቸው

“በአሁኑ ወቅት በአማራ ክልል ሰላም እንዲናጋ ህወሀት ምክንያት ሊሆን አይችልም፡፡መወቀስም መሞገስም ካለበት በክልሉ ነው፡፡ከመጠን በላይ በበዛ ጥላቻ የአማራ ክልልን ለማመስ የሚደረገው ጥረት መልሶ ራሱን ወደጥፋት የሚያመራ ድርጊት ነው››

ገዱ አንዳርጋቸው ዛሬ ሀምሌ 5/2010 ዓም

ያኔ በረከት ያሰለጠነውን ነውኮ ዛሬ ያንቆረቆረው ወገኖች! ብአዴን ብአዴን ነው። ትህነግን ለመከላከል የሚያደርገውን ያህል ወክያለሁ ለሚለው ሕዝብ ተናግሮ አያውቅም። አብዲ ኤሊ እንኳን እነ ጌታቸው አሰፋን ሲዘልግ እነሱ መደገፍ ልምድ ሆኖባቸዋል። ብአዴን (ብላው አውድመው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ) ጋር ወደፊት መሄድ አይቻልም።

ይህ የሚሊሻ ጥርቅም ፖለቲካ አስቦ መስራት አይችልም። ብአዴን ታዝዞ መግደልን ልምድ ያደረገ የሚሊሻ ድርጅት ነው። እንግዲህ ገዱ አማራ ላይ የተፈፀመውን ይሸከም። ቃሉን ይጠብቅ። ሕወሓትን እንኳ እሱ አያድነውም። የአማራን ሕዝብ ስለ ትህነግ/ህወሓት መልካም ነገር ሰብኮ ሊያስወድደው አይችልም። ከንቱ ድካም ነው። በዚህ ከቀጠለ ነገ እነ በረከት ይታደናታል! ይህ ሚሊሻ አስተሳሰቡ አያድነውም! ብአዴን አይድንም! የበረከትን መልሶ እየደገመ ሊቀጥል አይችልም!


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE