አፋር ከትግራይ ጋር ሊቀላቀል ነው የሚለው የሕወሓት ኘሮፖጋንዳ የቅጥፈት ወሬ ነው

የቅጥፈት ወሬ ነው

ሰሞኑን በፌስቡክ መንደር መነጋገሪያ የሆነ የአፋር ክልል ከትግራይ ክልል ጋር ሊቀላቀል ነው የሚል ሐሰተኛ ወሬ እየተነዛ ብዙዎች እውነት መስሏቸው ከፍተኛ ንትረክ ውስጥ ገብተው ጉዳዩ በርካቶችን ስሜት ውስጥ እያስገባ ሲሆን ቀሪዎች ደግሞ ድሮም የአፋር መሪ ድርጅት አብዴፓ መሪዎች የህወሓት ሚሊሽያ ነበሩ አሁንም ቢሆን በነሱ መሪነት ክልሎች ሊወሃዱ ይችላሉ ።የሚለው አቋም የያዙም አሉ፡፡

ሁለቱም በማይሆን ነገር ነገር ውስጥ ገብተው የዳኛ ያለህ እያሉ ነው፡፡ በውስጥ መስመር ያነጋገሩኝ ወንድሞቻችንም አሉ፡፡ ስለዚህ ስለሐሰተኛ መረጃ አንድ ነገር ለማለት ወደድኩኝ፡፡ በእርግጥ አፋርና የትግራይ ጎራቤቶች ናቸው፡፡ በጎርብትና ክልሎች ብቀላቀሉ አፋር ከትግራይ ይልቅ ከአማራ ጋር ብወሃድ ለአማራ ቅርብ ነው፡፡ ማለትም ከትግራይ ጋር አምስት በታች የሆነ ወረዳ የሚጎራበት ሲሆን ከአማራ ጋር ግን ከአስራ አምስት ወረዳ በላይ የሆነ ሰፊ ጎርብትና ስላለው የመወሃዱ ሂደት ብፈላግ ከትግራይ ይልቅ አማራ በመልካ ምድራዊ አቃማመጥ የተሻለ መሆኑን መረዳት ይቻላል ማለቴ ነው፡፡

ሌላው ህወሓትና የአፋሩ #አህዲድ (T-Qade) ከአንድ ምንጭ ናቸውና ክልሎች ሊያወህዱ ይችላሉ ለሚለው መላምት ምላሹ በእርግጥ ህወሐትና አህድድ የአንድ ሳንቲም ገፅታ ነው፡፡ ነገር ግን በዛው ልክ በአፋር ምድር ሁለቱን ድርጅቶች ማለትም (ህወሐትና አህዲድ) በትግሉ ዘመን የሚቃወሙ በርካታ ጦርነቶች በእነሱ ላይ ያወጁ ለ17 አመታት እነሱን ሲዋጉ የቆዩ የአፋር ድርጅቶች ነበሩ፡፡ እነሱም ኡጉጉሞ እና  የአፋር ነፃ አውጭ (አብነግ) ናቸው፡፡

በነሱ መሃል በተደረገው ጦርነት በርካታ መቶዎች የሚሆኑ ሠዎች ሙተዋል፡፡ የህወሓትና የአህዲድ ፍቅር ህዝብን እስከ መቀላቀል ቀርቶ አሁን አሁን ከጓዳ የሚያልፍ ሊሆን አይችልም፡፡ አፋር ከሌሎች ክልሎች ጋር ተቀላቅሎ(ተበታትኖ ) 48 አመታት መብቱ ተነፍጎ የሌሎች የበታች በመሆን ለግማሽ ምዕተ አመታት ለመብቱ እየታገለ የኖረ ህዝብ ነው፡፡

በልጆቹ ደም ያመጣው እድል ምንም እንኳን ልክ እንደሌሎች ክልሎች ህዝቦች በህወሓት መራሹ ቡዱን የአፋር ክልልም በርካታ ተፅዕኖ የደረሰበት ቢሆንም አሁን ግን ራሱን ከህወሓት ተፅዕኖ በአፋር ወጣቶች ትግል ነፃ ለመውጣት እየታገለ ይገኛል፡፡ ስለዚህ አፋር ከትግራይ ጋር ሊቀላቀል ነው የሚለው ኘሮፖጋንዳ የሐሳት የጠላት ወሬ መሆኑን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ፡፡