የ2012 የዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች ለ2 ወራት ተምረው እንዲመረቁ አቅጣጫ ተቀመጠ

የ2012 የዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች ለ2 ወራት ተምረው እንዲመረቁ አቅጣጫ ተቀመጠ

በኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ወረርሽኝ ምክንያት ትምህርት አቋርጠው በቤታቸው የሚገኙ የመጀመሪያ ዲግሪ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራቂ ተማሪዎችን ያቋረጡትን ትምህርት ከ45 ቀን እስከ 2 ወር በሆነ ጊዜ ውስጥ ተምረው በማጠናቀቅ እንዲመረቁ አቅጣጫ መቀመጡን ‘አዲስ ማለዳ ጋዜጣ‘ በዛሬው ዕትሙ መረጃውን ይዞ ወጥቷል።

የኢፌዴሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እንደገለፀው ከተመራቂ ተማሪዎች በተጨማሪ ሌሎች በየደረጃው ያሉ ተማሪዎች በተቀመጠው ጊዜ ያለፋቸውን ትምህርት አጠናቀው ወደ 2013 የትምህርት ዘመን እንዲሸጋገሩ ውሳኔ ላይ መደረሱን ለማወቅ ተችሏል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ የተቀመጠው አቅጣጫ ተማሪዎች መቼ ወደ ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚመለሱ ቀን እንዳልተቆረጠለት ተመላክቷል። ይህ የሆነበት ምክንያት ተማሪዎቹ መቼ ወደ ዩኒቨርሲቲ መመለስ እንዳለባቸው ኮቪድ-19 ያለበትን ደረጃ ያገናዘበ የመንግስትን ውሳኔ የሚፈልግ ጉዳይ በመሆኑ ነው ተብሏል።