በቤኒሻንጉል በንጹሐን ዜጎች ላይ የደረሰው ጥቃት ህወሓት ሀገርን ለማተራመስ እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ አካል ነው – አቶ አገኘው ተሻገር


ኢትዮጵያን ካጋጠሟት እጅግ ውስብስብ ችግሮች ለማዳን የተለያዩ ጠቃሚ ሃሳቦችን እና ገንቢ ትችቶችን የሚያቀርቡ ነፃ ሚዲያዎች ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ ይታወቃል። ስለዚህም ኢትዮ360፣ መረጃ ቲቪ፣ አዲስ ድምጽ፣ ምንሊክ ቲቪ እና ሌሎችም የኢትዮጵያዊነት አጀንዳ የሚያራምዱ ሚዲያዎች በመተባበር ፕሮግራሞቻቸውን በሳተላይት ቲቪ ለኢትዮጵያ ህዝብ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ሚዲያዎች የፈጠሩት ማህበር የሳተላይት ወጪውን መሸፈን እንዲያስችለው ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ ከፍተናል → እዚህ ሊንክ ላይ ይጫኑ። ለትብብርዎ እናመሰግናለን።
በጉባ ወረዳ በንጹሐን ዜጎች ላይ ጥቃት የፈጸሙ ኃይሎች በህውሓት የስልጠና እና የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያገኙ ተጠቆመ
Image may contain: 1 person, suit(ኢ ፕ ድ) – በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ጉባ ወረዳ በንጹሐን ዜጎች ላይ ጥቃት ያደረሰው ታጣቂ ኃይል በህውሓት ስልጠናና የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያገኙ የአማራ ክልል አስታወቀ። ዓላማው በብሄር ብህረሰቦች መካከል ግጭት በመፍጠር የአካባቢውን ሰላም ለማወክ መሆኑም ተመለከተ።
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈትቤት ኃላፊ አቶ አገኘው ተሻገር በጥቃቱ ዙሪያ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ ጥቃቱን የፈጸመው ኃይል በአካባቢው የብሔር ግጭት የመቀስቀስ ዓላማ በመያዝ ተደጋጋሚ የጥፋት ሙከራ ሲያደርግ የቆየ ነው።
ታጣቂ ኃይሉ በህውሓት የስልጠናና የገንዘብ ድጋፍ እንደሚደረግለት አመልክተው፤ ህውሓት ሀገርን ለማተራመስ እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ አካል መሆኑምን ጠቁመዋል። ድርጊቱ ከተፈጸመበት ጊዜ ጀምሮ አጥፊዎችን ፈልጎ ለመያዝና አስፈላጊውን ዕርምጃ ለመውሰድ የፀጥታ መዋቅሩ የተጠናከረ ጥረት እያደረገ መሆኑንም አስታውቀዋል ።በአሁኑ ጊዜም አካባቢው ላይ ሰላም ሰፍኗል። አርሶአደሩም የእርሻ ሥራውን በማከናወን ላይ ይገኛል ብለዋል፡